Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 38:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 የመታጠቢያውን ሳሕንና ማስቀመጫውን ጭምር ከነሐስ ሠራ፤ ነሐሱም የተገኘው በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ የሚያገለግሉ ሴቶች ካመጡት የነሐስ መስተዋቶች ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 የናስ መታጠቢያ ሳሕንና የንሓስ መቆሚያውን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ ከሚያገለግሉት ሴቶች መስተዋት ሠሩት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 የነሐሱ የመታጠቢያ ሳሕንና የነሐሱ ማስቀመጫውን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ከሚያገለግሉ ሴቶች መስተዋት ሠራ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 የመ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ውን ሰንና መቀ​መ​ጫ​ው​ንም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ከሚ​ያ​ገ​ለ​ግሉ ከሴ​ቶች መስ​ተ​ዋት ከናስ አደ​ረገ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 የመታጠቢያውን ሰንና መቀመጫውንም በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ከሚያገለግሉ ከሴቶች መስተዋት ከናስ አደረገ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 38:8
23 Referencias Cruzadas  

ሑራም ለእያንዳንዱ የዕቃ ማስቀመጫ ዐሥር መታጠቢያ ገንዳዎች ሠራ፤ እያንዳንዱ ገንዳ ዙሪያ አጋማሽ ስፋት አንድ ሜትር ከሰማንያ ሳንቲ ሜትር ያኽል ሲሆን፥ ስምንት መቶ ሊትር ያኽል ውሃ ይይዝ ነበር፤


እንዲሁም ጥልቀቱ ሁለት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር፥ የጐኑ አጋማሽ አራት ሜትር ከአርባ ሳንቲ ሜትር፥ ዙሪያው ዐሥራ ሦስት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር የሆነ ክብ ገንዳ አሠራ፤


እግዚአብሔር ሆይ! ንጹሕነቴን ለማሳየት እጆቼን እታጠባለሁ፤ መሠዊያህንም በመዞር አንተን አመልካለሁ።


እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤


ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነው መሠዊያና ለእርሱ የሚያስፈልገው ነገር ሁሉ፥ የመታጠቢያው ሳሕንና ማስቀመጫው፥


በመሠዊያው ጐንና ጐን ባሉት ቀለበቶችም ውስጥ አስገባቸው፤ መሠዊያው ከሳንቃ የተሠራ ሆኖ ውስጡ ክፍት ነበር።


የመታጠቢያውን ሣሕን በድንኳኑና በመሠዊያው መካከል አስቀምጠህ ውሃ ሙላበት።


እኔን የሚያዳምጥ፥ በየቀኑ በደጃፌ ላይ ተግቶ የሚገኝ፥ በቤቴ መግቢያ አጠገብ የሚጠባበቀኝ ሰው የተባረከ ነው።


የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “በዚያን ጊዜ ለዳዊት ልጆችና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ከኃጢአታቸውና ከርኲሰታቸው የሚያነጻ ምንጭ ይከፈታል።


ጴጥሮስ ከቤት ውጪ በሊቀ ካህናቱ ግቢ ውስጥ ተቀምጦ ነበር፤ በዚያን ጊዜ አንዲት ገረድ ወደ እርሱ ቀርባ “አንተም ከገሊላዊው ኢየሱስ ጋር ነበርክ!” አለችው።


ከዚህም በኋላ ዕድሜዋ ሰማኒያ አራት ዓመት እስኪሆን ድረስ ከቤተ መቅደስ ሳትለይ በጾምና በጸሎት ቀንና ሌሊት እግዚአብሔርን ታገለግል ነበር።


ኢየሱስም “ሰውነቱን የታጠበ ሁለመናውም ንጹሕ በመሆኑ እግሩን ከመታጠብ በቀር ሌላ አያስፈልገውም፤ እናንተም ንጹሖች ናችሁ፤ ነገር ግን ሁላችሁም ንጹሖች አይደላችሁም” አለው።


ጴጥሮስ ግን በውጭ በበሩ አጠገብ ቆሞ ነበር፤ በካህናት አለቃው የታወቀው ደቀ መዝሙር መጣና ለበረኛይቱ ልጃገረድ ነግሮ ጴጥሮስን አስገባው፤


በእርግጥ መበለት የሆነችና ብቻዋን የምትኖር፥ ተስፋዋን በእግዚአብሔር ላይ አድርጋ ሌሊትና ቀን የእግዚአብሔርን ርዳታ በመለመን በጸሎት ጸንታ ትኖራለች።


እነዚህ ነገሮች የመታደስ ጊዜ እስኪመጣ ድረስ በሥራ ላይ የዋሉ አፍአዊ ሥርዓቶች ናቸው፤ እነርሱ ስለ መብልና ስለ መጠጥ፥ ስለ ልዩ ልዩ የመንጻት ሥርዓቶችም ብቻ የተደረጉ ናቸው።


ልጆች ሆይ! ማንም አያታላችሁ፤ ክርስቶስ ጻድቅ እንደ ሆነ ጽድቅን የሚያደርግ ሁሉ ጻድቅ ነው።


እነሆ ዔሊ በዕድሜው አርጅቶ ነበር፤ ልጆቹም በእስራኤላውያን ላይ የሚያደርጉት ክፉ ነገርና በድንኳኑ ደጃፍ ከሚያገለግሉት ሴቶች ጋር እንደሚያመነዝሩ ሰማ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos