Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 25:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 “ርዝመቱ መቶ ኻያ አምስት ሳንቲ ሜትር፥ የጐኑም ስፋት ሰባ አምስት ሳንቲ ሜትር የሆነም የስርየት መክደኛ ሥራለት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 “ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፣ ወርዱ አንድ ክንድ ተኩል የሆነ የስርየት መክደኛ ከንጹሕ ወርቅ ሥራለት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ከንጹሕ ወርቅ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወርዱ አንድ ክንድ ተኩል የሆነ የስርየት መክደኛ ሥራ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ከጥሩ ወር​ቅም ርዝ​መቱ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወር​ዱም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ የስ​ር​የት መክ​ደኛ ሥራ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ከጥሩ ወርቅም ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ የስርየት መክደኛ ሥራ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 25:17
12 Referencias Cruzadas  

ዳዊት ለልጁ ለሰሎሞን የቤተ መቅደሱን የዕቃ ግምጃ ቤቶቹን፥ በደርቡና በምድር ቤቱ የሚገኙትን ክፍሎችና ኃጢአት የሚሰረይበትን የቅድስተ ቅዱሳኑን አሠራር የሚገልጥ ዕቅድ ሰጠው።


ከተቀጠቀጠም ወርቅ ክንፎች ያሉአቸው የሁለት ኪሩቤል ምስል ሥራ፤


ከዚህ በኋላ የቃል ኪዳኑን ታቦት በስርየት መክደኛው ክደነው፤


የኪዳኑን ታቦት፥ መሎጊያዎቹን፥ የስርየት መክደኛውንና የታቦቱ መሸፈኛ የሆነውን መጋረጃ፥


ርዝመቱ መቶ ዐሥር ሳንቲ ሜትር ስፋቱም ሥልሳ ስድስት ሳንቲ ሜትር የሆነ የስርየት መክደኛ ከንጹሕ ወርቅ ሠራ፤


ሁለቱንም የድንጋይ ጽላቶች ወስዶ በቃል ኪዳኑ ታቦት ውስጥ አስቀመጣቸው፤ መሎጊያዎችንም በታቦቱ ቀለበቶች ውስጥ አስገባ፤ የስርየት መክደኛውንም በታቦቱ ላይ አኖረ፤


አንተን እንደ ጠባቂ ኪሩብ አድርጌ በመሾም በዚያ መደብኩህ፤ በተቀደሰው ተራራዬ ላይ ትኖር ነበር፤ እጅግ በሚያብረቀርቁ የከበሩ ድንጋዮች መካከል ትመላለስ ነበር።


እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበው በእርሱ የሚያምኑ ሁሉ በደሙ የኃጢአታቸውን ስርየት እንዲያገኙ ነው፤ እግዚአብሔር ይህን ማድረጉ በትዕግሥቱ የቀድሞውን ኃጢአት እንዳልነበረ በማድረግ የራሱን ትክክለኛ ፍርድ ለመግለጥ ነው።


እንግዲህ ምሕረት እንድንቀበልና ርዳታ በሚያስፈልገን ጊዜ ጸጋ እንድናገኝ ጸጋው ወደሚገኝበት ወደ እግዚአብሔር ዙፋን ያለ አንዳች ፍርሀት እንቅረብ።


በታቦትዋም ላይ ያለውን የኃጢአት ማስተስረያ መክደኛ በክንፋቸው የሚጋርዱ የክብር ኪሩቤል ነበሩ፤ ነገር ግን ስለ እነዚህ ነገሮች ሁሉ አሁን በዝርዝር መናገር አንችልም።


እርሱም ኃጢአታችንን ይደመስሳል፤ የእኛ ኃጢአት ብቻ ሳይሆን የዓለሙም ሁሉ ኃጢአት የሚደመሰሰው በእርሱ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos