17 መርዶክዮስም ተነሥቶ ሄደ፤ አስቴር በነገረችውም መሠረት ሁሉን ነገር አደረገ።
17 ስለዚህ መርዶክዮስ ሄደ፤ የአስቴርንም ትእዛዝ ሁሉ ፈጸመ።
17 መርዶክዮስም ሄዶ አስቴር እንዳዘዘችው ሁሉ አደረገ።
“ሄደህ በሱሳ የሚገኙትን አይሁድ በአንድነት ሰብስብ፤ ጾም ዐውጃችሁም ለእኔ ጸልዩ፤ እስከ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ምንም ዐይነት ምግብ አትብሉ፤ ምንም ዐይነት መጠጥ አትጠጡ፤ እኔና ደንገጡሮቼም በዚሁ ዐይነት እንቈያለን፤ ከዚህም በኋላ በሕግ የተከለከለ ቢሆንም ደፍሬ ወደ ንጉሡ ዘንድ እገባለሁ፤ ይህን በማድረጌ ብሞትም ልሙት።”
ጾም በጀመረች በሦስተኛውም ቀን አስቴር ልብሰ መንግሥትዋን ለብሳ በዙፋኑ ክፍል ፊት ለፊት ወደሚገኘው ወደ ውስጠኛው የቤተ መንግሥት አደባባይ ገብታ ቆመች፤ ንጉሡም በዚያው ክፍል ውስጥ ከመግቢያው በር ፊት ለፊት በተዘረጋ ዙፋን ላይ ተቀምጦ ነበር።