Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




አስቴር 2:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ስለዚህም አርጤክስስ በነገሠ በሰባተኛው ዓመት ቴቤት ተብሎ በሚጠራው በዐሥረኛው ወር አስቴር ወደ ቤተ መንግሥቱ ተወሰደች።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 በነገሠ በሰባተኛው ዓመት ቴቤት በተባለው በዐሥረኛው ወር አስቴር ወደ ንጉሥ ጠረክሲስ ቤተ መንግሥት ተወሰደች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 አርጤክስስም በነገሠ በሰባተኛው ዓመት አዳር በሚባለው በአሥራ ሁለተኛው ወር አስቴር ወደ ንጉሡ ቤት ተወሰደች።

Ver Capítulo Copiar




አስቴር 2:16
7 Referencias Cruzadas  

ይልቁንም አርጤክስስ ንጉሠ ነገሥት በሆነበት ዘመን መጀመሪያ ላይ፥ ጠላቶቻቸው በይሁዳና በኢየሩሳሌም ይኖሩ በነበሩት እስራኤላውያን ላይ በጽሑፍ የተቀናበረ ክስ መሠረቱባቸው።


ዕዝራ ንጉሡ አርጤክስስ በነገሠ በሰባተኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ወደ ኢየሩሳሌም ደረሰ።


ዘግየት ብሎም የንጉሡ ቊጣ ከበረደ በኋላ እንኳ፥ ንግሥት አስጢን ስላደረገችው ነገርና በእርስዋም ላይ ስለ ተላለፈው ዐዋጅ ማሰላሰሉን ቀጠለ።


በዚህ ዐይነት አስቴር ወደ ንጉሡ ፊት የምትቀርብበት ጊዜ ደረሰ፤ ይህችም አስቴር የአቢኀይል ልጅ፥ እንደ ልጁ አድርጎ ያሳደጋት የመርዶክዮስ የአጐት ልጅ የነበረችውና ባያት ሁሉ ዘንድ ሞገስን ያገኘች ነበረች፤ እርስዋም ወደ ንጉሡ ፊት የመቅረብ ተራዋ በደረሰ ጊዜ የለበሰችው፥ የምርጥ ሴቶች መኖሪያ ቤት ኀላፊ የነበረው ጃንደረባው ሄጋይ እንድትለብስ የመከራትን እንጂ እርስዋ የጠየቀችውን ልብስ አልነበረም።


ንጉሡም ከሌሎቹ ልጃገረዶች ሁሉ አስበልጦ ወደዳት፤ ከሌሎቹም ሁሉ ይበልጥ በፊቱ ሞገስንና መወደድን አገኘች፤ እርሱም መንግሥታዊውን ዘውድ አንሥቶ በራስዋ ላይ ደፋላትና በአስጢን ቦታ አነገሣት።


በንጉሠ ነገሥትህ ግዛት በየአገሩ ባለ ሥልጣኖችን በመሾም ውብ የሆኑትን ልጃገረዶች እየመረጡ መናገሻ ከተማ በሆነችው በሱሳ ውስጥ ለአንተ የተመረጡ ሴቶች መኖሪያ ወደ ሆነው ቤት እንዲያመጡአቸው ይደረግ፤ የዚህም ቤት ኀላፊ ባደረግኸው በጃንደረባው ሄጋይ ቊጥጥር ሥር ይጠበቁ፤ የቊንጅናም እንክብካቤ ይደረግላቸው።


ይህም የሆነው ሲዋን ተብሎ የሚጠራው ሦስተኛ ወር በገባ በሃያ ሦስተኛው ቀን ነበር፤ መርዶክዮስ የንጉሡን ጸሐፊዎች ሁሉ ጠርቶ ለአይሁድ፥ ከሕንድ እስከ ኢትዮጵያ ያሉትን መቶ ኻያ ሰባት አገሮች ለሚያስተዳድሩ አገረ ገዢዎችና ሌሎችም ባለሥልጣኖች የሚላኩ ደብዳቤዎችን አስጻፈ፤ ደብዳቤዎቹም በእያንዳንዱ አገር ቋንቋና የአጻጻፍ ሥርዓት እንዲሁም በአይሁድ ቋንቋና የአጻጻፍ ሥርዓት ተከትለው እንዲጻፉ ተደረገ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos