አስቴር 2:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 እርስዋም ሌሊቱን ከንጉሡ ጋር ዐድራ በማግስቱ ወደ ሌላ የምርጥ ሴቶች መኖሪያ ቤት ትወሰዳለች፤ እዚያም የንጉሡ ቊባቶች ኀላፊ በሆነው በጃንደረባው በሻዕሸጋዝ ቊጥጥር ሥር ትሆናለች፤ በንጉሡ ዘንድ ተወዳጅነትን አግኝታ እርሱ ስምዋን ጠርቶ እንደገና እንድትመጣለት ካልጠየቀ በቀር ዳግመኛ ወደ እርሱ አትቀርብም። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 ሲመሽ ወደዚያው ትሄዳለች፤ ሲነጋም የቁባቶች ኀላፊ በሆነው በንጉሡ ጃንደረባ በሻአሽጋዝ ጥበቃ ሥር ወደሚገኘው ወደ ሌላው የሴቶች መጠበቂያ ቤት ትመለሳለች፤ ደስ የተሠኘባት ካልሆነችና በስሟም ካልጠራት ዳግመኛ ወደ ንጉሡ ዘንድ አትገባም። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 ማታም ትገባ ነበር፥ ሲነጋም ተመልሳ ወደ ሁለተኛው ሴቶች ቤት ቁባቶችን ወደሚጠብቅ ወደ ንጉሡ ጃንደረባ ወደ ጋይ ትመጣ ነበር፥ ንጉሡም ያልፈለጋት እንደ ሆነ፥ በስምዋም ያልተጠራች እንደሆነ፥ ከዚያ ወዲያ ወደ ንጉሡ አትገባም ነበር። Ver Capítulo |