አስቴር 1:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 የአትክልት ቦታውም ከነጭ ጥጥ በፍታ በተሠሩ ሰማያዊ ቀለም ባላቸው መጋረጃዎች የተጌጠ ነበር፤ መጋረጃዎቹም ከሐምራዊ በፍታ በተሠሩና የብር ቀለበት በተበጀላቸው ገመዶች በዕብነ በረድ ምሰሶዎች ላይ ተንጠልጥለው ነበር፤ ከወርቅና ከብር የተሠሩ ድንክ አልጋዎችም ነጭና ቀይ፥ ቢጫና ሰማያዊ ቀለማትን በሚፈነጥቅ የዕብነ በረድ ወለል ላይ ተደርድረው ነበረ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 አደባባዩም ከነጭና ከሰማያዊ በፍታ የተሠሩ መጋረጃዎች ነበሩት፤ እነርሱም የብር ቀለበት በተበጀላቸው፣ ከነጭ በፍታና ከሐምራዊ ቀለም በተሠሩ ገመዶች በዕብነ በረዱ ምሰሶዎች ላይ ተንጠልጥለው ነበር። ነጭና ቀይ ቀለማት ተሰበጣጥረው በተነጠፉበት ወለል ላይ የወርቅና የብር ድንክ ዐልጋዎች ነበሩ፤ እነርሱም ከዕብነ በረድ፣ ቀስተ ደመና ከሚመስሉ ቀለሞችና ከሌሎች የከበሩ ድንጋዮች የተሠሩ ነበሩ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 ነጭ፥ አርንጓዴ፥ ሰማያዊም መጋረጆች ከጥሩ በፍታና ከሐምራዊ ግምጃ በተሠራ ገመድ፥ በብር ቀለበትና በዕብነ በረድ አዕማድ ላይ ተዘርግተው ነበር፥ አልጋዎቹም ከወርቅና ከብር ተሠርተው በቀይና በነጭ በብጫና በጥቁር ዕብነ በረድ ወለል ላይ ነበሩ። Ver Capítulo |