Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤፌሶን 3:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እንግዲህ በእግዚአብሔር አብ ፊት በጒልበቴ ተንበርክኬ የምጸልየው በዚህ ምክንያት ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 በዚህም ምክንያት በአብ ፊት እንበረከካለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 በዚህም ምክንያት ከአብ ፊት እንበረከካለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ስለ​ዚ​ህም በል​ቡ​ናዬ ተን​በ​ር​ክኬ ለአብ እሰ​ግ​ዳ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14-15 ስለዚህ ምክንያት በሰማይና በምድር ያለ አባትነት ሁሉ ከሚሰየምበት ከአብ ፊት እንበረከካለሁ፤

Ver Capítulo Copiar




ኤፌሶን 3:14
16 Referencias Cruzadas  

ኑ፤ ዝቅ ብለን እንስገድ! በፈጣሪያችን በእግዚአብሔር ፊት እንንበርከክ!


ስለዚህ ለኢየሱስ ስም ክብር፥ በሰማይና በምድር፥ ከምድር በታችም ያሉት ሁሉ በጒልበታቸው ይንበረከካሉ።


እዚያ የምንቈይበት ጊዜ ሲያልቅ ተለይተናቸው ጒዞአችንን ቀጠልን፤ ሁሉም ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር ሆነው እስከ ከተማው ውጪ ድረስ ሸኙን፤ በባሕሩም ዳር ተንበርክከን ከጸለይን በኋላ ተሰነባበትን።


በሰማይ ባለው መንፈሳዊ በረከት ሁሉ በክርስቶስ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን።


ዳንኤል ዐዋጁ ተፈርሞበት እንደ ጸና ቢያውቅም እንኳ ወደሚኖርበት ሰገነት ወጣ፤ የሚኖርበትም ሰገነት በኢየሩሳሌም ትይዩ የተከፈቱ መስኮቶች ነበሩት፤ ከዚህ በፊት ያደርገው እንደ ነበረም በጒልበቱ በመንበርከክ አምላኩን እያመሰገነ በቀን ሦስት ጊዜ ይጸልይ ነበር።


የምሽትም መሥዋዕት የሚቀርብበት ሰዓት በደረሰ ጊዜ በሐዘን ከተቀመጥኩበት ስፍራ ተነሣሁ፤ የቀደድኩትን ልብስ እንደ ለበስኩ፥ በጒልበቴም በመንበርከክ ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሔር እጆቼን ዘርግቼ እንዲህ ስል ጸለይኩ፦


የማይለወጥ እውነተኛ የተስፋ ቃል ስሰጥ በራሴ ምዬ ነው። ስለዚህ ጉልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፤ አንደበትም ሁሉ በእኔ ስም ይምላል።


ከዚህ በኋላ ጳውሎስ ከሁሉም ጋር ተንበርክኮ ጸለየ።


41 ከዚህ በኋላ የድንጋይ ውርወራ ያኽል ከእነርሱ ራቅ ብሎ ሄደ፤ ተንበርክኮም እንዲህ ሲል ጸለየ፦


ይሁን እንጂ ለእኔ ታማኞች የሆኑ፥ ለባዓል ያልሰገዱና ምስሉንም ያልተሳለሙ ሰባት ሺህ ሰዎችን በእስራኤል ምድር በሕይወት እንዲተርፉ አደርጋለሁ።”


ሰሎሞን ጸሎቱን ከፈጸመ በኋላ እጆቹን እንደ ዘረጋ ተንበርክኮ ከነበረበት መሠዊያ ፊት ተነሥቶ ቆመ።


ጴጥሮስ ግን ሁሉንም ወደ ውጪ አስወጣና ተንበርክኮ ጸለየ፤ ወደ አስከሬኑም መለስ አለና “ጣቢታ! ተነሺ!” አለ፤ እርስዋም ዐይኖችዋን ከፈተች፤ ጴጥሮስንም አየች፤ ተነሥታም ቁጭ አለች።


ተንበርክኮም “ጌታ ሆይ! ይህን በደል አትቊጠርባቸው!” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ፤ ይህንንም ብሎ ሞተ።


በሰማይና በምድር ያለ እያንዳንዱ ቤተሰብ እውነተኛ ስሙን የሚያገኘው ከእግዚአብሔር ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios