Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መክብብ 10:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ጒድጓድን የሚቈፍር ሰው ራሱ ይወድቅበታል፤ ቅጽርንም የሚያፈርስ በእባብ ይነደፋል፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ጕድጓድን የሚምስ ራሱ ይገባበታል፤ ቅጥርንም የሚያፈርስ እባብ ይነድፈዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ጉድጓድን የሚምስ ይወድቅበታል፥ ቅጥርንም የሚያፈርስን እባብ ትነድፈዋለች።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ለባ​ል​ን​ጀ​ራው ጕድ​ጓ​ድን የሚ​ምስ ይወ​ድ​ቅ​በ​ታል፥ ቅጥ​ር​ንም የሚ​ያ​ፈ​ር​ስን እባብ ትነ​ድ​ፈ​ዋ​ለች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ጕድጓድን የሚምስ ይወድቅበታል፥ ቅጥርንም የሚያፈርስን እባብ ትነድፈዋለች።

Ver Capítulo Copiar




መክብብ 10:8
13 Referencias Cruzadas  

ለሌሎች ወጥመድን የሚዘረጉ ሰዎች ራሳቸው ይያዙበታል፤ በሰው ላይ የሚሰዱት የድንጋይ ናዳ እነርሱን መልሶ ይጐዳቸዋል።


ስለዚህም ሃማን መርዶክዮስን ለመስቀል ባዘጋጀው እንጨት ላይ ተሰቀለ፤ ከዚያም በኋላ የንጉሡ ቊጣ በረደ።


በቀርሜሎስ ተራራ ላይ ወጥተው ቢሸሸጉም ተከታትዬ ከዚያ አወጣቸዋለሁ፤ ወደ ጥልቅ ባሕር ገብተው ከእኔ ለመሰወር ቢሞክሩም እንዲነድፋቸው የባሕሩን ዘንዶ አዛለሁ።


ያ ቀን አንድ ሰው ከአንበሳ ሸሽቶ ሲሄድ ድብ እንደሚያጋጥመው፥ ወይም አምልጦ ወደ ቤቱ ሲገባ እጁን በግድግዳ ላይ ቢያሳርፍ እባብ እንደሚነድፈው ሁኔታ ይሆንባችኋል።


አኪጦፌል የሰጠው ምክር ተቀባይነት እንዳላገኘ በተረዳ ጊዜ አህያውን ጭኖ ወደ መኖሪያ ከተማው ተመልሶ ሄደ፤ ሁሉን ነገር መልክ በማስያዝ ካስተካከለም በኋላ ተሰቅሎ ሞተ፤ በቤተሰቡም መቃብር ተቀበረ።


ወደ አባቱ ቤት ወደ ዖፍራም ሄዶ የጌዴዎን ልጆች የሆኑትን ሰባውን ወንድሞቹን በአንድ ድንጋይ ላይ ዐረዳቸው፤ የጌዴዎን መጨረሻ ልጅ ኢዮአታም ግን ተደብቆ ስለ ነበር ከሞት ተረፈ፤


ከዚያም በኋላ የኢዮአብ አጃቢዎች ከሆኑ ወታደሮች ዐሥሩ ወደ አቤሴሎም ሄደው ዙሪያውን በመክበብ በጦር መሣሪያ ገደሉት።


ጠላቶቼ እኔን ለመያዝ ወጥመድ ዘርግተውብኛል፤ ሁለንተናዬን የሚያጐብጥ ተስፋ መቊረጥ ደረሰብኝ፤ በመንገዴ ጒድጓድ ቈፈሩ፤ ነገር ግን እነርሱ ራሳቸው ወደቁበት።


ቅን ሰው በደግነቱ ይድናል፤ እምነት የማይጣልበት ሰው ግን የራሱ ክፉ ምኞት ወጥመድ ሆኖ ይይዘዋል።


ድንጋይን የሚፈነቅል በፈነቀለው ድንጋይ ራሱ ይጐዳል፤ እንጨትን የሚፈልጥ በፈለጠው እንጨት ይቈስላል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios