Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መክብብ 10:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 በዓለም ላይ ሌላም ክፋት አይቻለሁ፤ ይኸውም ገዢዎች የሚፈጽሙት ግፍ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ከፀሓይ በታች ያየሁት ክፉ ነገር አለ፤ ይህም ከገዥ የሚወጣ ስሕተት ነው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ከፀሐይ በታች ያየሁት ክፉ ነገር አለ፥ እርሱም ከገዢ የሚወጣ ስሕተት ነው፥

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ከፀ​ሓይ በታች ያየ​ሁት ክፉ ነገር አለ፥ እር​ሱም ከገዢ ባለ​ማ​ወቅ የሚ​ወጣ ስሕ​ተት ነው፥

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ከፀሐይ በታች ያየሁት ክፉ ነገር አለ፥ እርሱም ከገዢ የሚወጣ ስሕተት ነው፥

Ver Capítulo Copiar




መክብብ 10:5
10 Referencias Cruzadas  

በዚህ ዓለም እጅግ የሚያሳዝን ክፉ ነገር ደግሞ አየሁ፤ ይኸውም ሰዎች ለክፉ ቀን ይጠቅመናል ብለው ሀብት ያከማቻሉ፤ ነገር ግን በአንድ መጥፎ አጋጣሚ ሀብታቸውን ያጡና ለልጆቻቸው የሚተላለፍ ምንም ነገር ሳይተርፋቸው ይቀራል።


የሁሉም ዕድል ፈንታው አንድ ዐይነት ነው፤ ይህም በዓለም እንደሚደረገው እንደማንኛውም ነገር ሁሉ እጅግ የከፋ ነው፤ ሰዎችም በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ አእምሮአቸው በክፋትና በእብደት የተሞላ ሆኖ በመጨረሻ ይሞታሉ።


በዚህ ዓለም በሰው ሁሉ ላይ የሚደርስ እጅግ የከፋ ነገር ተመለከትኩ።


በዚህ ዓለም ያለውን ሌላውንም ከንቱ ነገር ተመለከትኩ፤


እንደገናም በዓለም ያለውን የፍርድ መጓደልና ግፍ ተመለከትኩ፤ የተገፉ ጭቊኖች የሚያጽናናቸው አጥተው ያለቅሱ ነበር፤ የፈላጭ ቈራጭነት ሥልጣን በገዢዎቻቸው እጅ ስለ ሆነ የሚረዳቸው አላገኙም።


ደግሞም በዓለም ላይ በቅንነትና በፍትሕ ቦታ ዐመፅና ግፍ መብዛቱን አየሁ።


ደጋግ ሰዎች ድል በሚያደርጉበት ጊዜ ሰው ሁሉ ይደሰታል፤ ክፉ ሰዎች ሥልጣን በሚይዙበት ጊዜ ግን ሰው ሁሉ በሐዘን አንገቱን ይደፋል።


ጸጥ ብለህ ብትታገሥ ከባድ ለሆነው በደልህ እንኳ ይቅርታ ማግኘት ስለምትችል አለቃህ በተቈጣህ ጊዜ የሥራ ቦታህን አትልቀቅ፤


ሞኞች ከፍተኛ ሥልጣን ሲያገኙ ባለጸጎች ግን ችላ ተብለው ዝቅተኛ ስፍራ ይዘዋል።


ሞኞች በድሎት መኖር አይችሉም፤ የባሪያ በመኳንንት ላይ ገዢ መሆንማ ምንኛ የከፋ ነው?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios