Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘዳግም 9:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 “ስለዚህም ቃል ኪዳኑ የተጻፈባቸውን ሁለቱን የድንጋይ ጽላቶች በሁለት እጆቼ እንደ ያዝኩ ከተራራው ተመልሼ ወረድኩ፤ በዚያን ጊዜ የእሳት ነበልባል ከተራራው ይታይ ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ስለዚህ ተራራው በእሳት እየተቀጣጠለ ሳለ፣ ሁለቱን የቃል ኪዳን ጽላት በሁለቱም እጆቼ እንደ ያዝሁ ከተራራው ተመልሼ ወረድሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 “ስለዚህ ተመልሼ ከተራራው ወረድሁ፥ ተራራውም በእሳት ይነድድ ነበር፤ ሁለቱም የቃል ኪዳን ጽላቶች በሁለቱ እጆቼ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 እኔም ተመ​ልሼ ከተ​ራ​ራው ወረ​ድሁ፤ ተራ​ራ​ውም በእ​ሳት ይነ​ድድ ነበር፤ ሁለ​ቱም የቃል ኪዳን ጽላት በሁ​ለቱ እጆች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 እኔም ተመልሼ ከተራራው ወረድሁ፥ ተራራውም በእሳት ይነድድ ነበር፤ ሁለቱም የቃል ኪዳን ጽላቶች በሁለቱ እጆቼ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 9:15
7 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር በእሳት ስለ ወረደበት መላው የሲና ተራራ በጢስ ተሞላ። ጢሱም ከእሳት ምድጃ እንደሚወጣ ዐይነት ሆኖ ወደ አየር ተትጐለጐለ፤ ሰዎቹም እጅግ ፈርተው ተንቀጠቀጡ።


ስለዚህ ሙሴ በትሩን አንሥቶ ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም ነጐድጓድና በረዶ መብረቅም ወደ ምድር አወረደ፤ በዚህ ዐይነት እግዚአብሔር በግብጽ ምድር ላይ በረዶን አዘነበ።


“እስከ ሰማይ በሚደርስ የእሳት ነበልባልና ጥቅጥቅ ባለ የጢስ ደመና ወደተጋረደው ተራራ ግርጌ ቀርባችሁ ቆማችሁ።


“ተራራው በእሳት ይነድ በነበረበት ወቅት ከጨለማው ውስጥ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ የነገድ አለቆችና መሪዎች ሁሉ ወደ እኔ መጥታችሁ፥


እናንተም እግዚአብሔር አምላካችሁ ከሰጣችሁ ትእዛዝ ወዲያው ፈቀቅ ብላችሁ፥ ወርቅ አቅልጣችሁ በጥጃ ምስል ጣዖት በመሥራት በእግዚአብሔር ላይ ማመፃችሁን ተመለከትኩ።


እናንተ በእጅ ወደሚዳሰሰው ወይም ወደሚቃጠለው ወደ ሲና ተራራ አልደረሳችሁም፤ ወደ ጭጋጉ፥ ወደ ጨለማውም፥ ወደ ዐውሎ ነፋሱም፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos