Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘዳግም 16:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 እግዚአብሔር የሚሰጥህን ምድር ወርሰህ በሕይወት መኖር ትችል ዘንድ ሁልጊዜ ቅንና ትክክለኛ ሁን።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 በሕይወት እንድትኖርና አምላክህ እግዚአብሔር የሚሰጥህን ምድር እንድትወርስ፣ የጽድቅ ፍርድን ብቻ ተከተል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 በሕይወት እንድትኖርና ጌታ እግዚአብሔር የሚሰጥህን ምድር እንድትወርስ ትክክለኛ፥ እውነተኛውንም ፍርድ ብቻ ተከተል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 በሕ​ይ​ወት ትኖር ዘንድ፥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ሰ​ጥ​ህን ምድር ትወ​ርስ ዘንድ እው​ነ​ተ​ኛ​ውን ፍርድ ተከ​ተል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 በሕይወት ትኖር ዘንድ፥ አምላክህ እግዚአብሔርም የሚሰጥህን ምድር ትወርስ ዘንድ እውነተኛውን ፍርድ ተከተል።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 16:20
9 Referencias Cruzadas  

አእምሮአችሁ በእነዚህ ከሁሉ በሚበልጡና በሚያስመሰግኑ መልካም ነገሮች የተመላ ይሁን፤ በመጨረሻም ወንድሞች ሆይ! እውነተኛ፥ ክቡር፥ ትክክለኛ፥ ንጹሕ፥ አስደሳችና ምስጉን የሆኑ ነገሮችን ሁሉ አስቡ።


ሕግን በመከተል ስለሚገኘው ጽድቅ ሙሴ የጻፈው “ሕግን የሚፈጽም ሁሉ በሕይወት ይኖራል” የሚል ነው።


እግዚአብሔር መልካም የሆነውንና ከአንተ የሚፈልገውን ነግሮሃል፤ ይኸውም ፍትሕን እንድትጠብቅ፥ ደግነትን እንድትወድ፥ ከአምላክህ ጋር በትሕትና እንድትመላለስ ነው።


እንዲህ ዐይነቱ ሰው ሕጌን ይፈጽማል፤ ሥርዓቴን ያከብራል፤ ያ ሰው ጻድቅ ስለ ሆነ በሕይወት ይኖራል፤ ይህን የተናገርኩ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ነኝ።


“ሰው ጻድቅ፥ ፍትሓዊና ትክክለኛ ቢሆን፥


ከዚህ በኋላ ሙሴ ለሕዝቡ እንዲህ አለ፤ “እስራኤል ሆይ፥ አሁን እንግዲህ የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር ገብታችሁ ለመውረስ ያበቃችሁ ዘንድ የማስተምራችሁን ሕግና ሥርዓት አዳምጣችሁ በሥራ ላይ አውሉት።


“ለአምላክህ ለእግዚአብሔር መሠዊያ በምትሠራበት አጠገብ የማምለኪያ ዐፀድ (ዛፍ) አትትከል።


መልካም ሥራ ለመሥራት ቊርጥ ውሳኔ ያደረገ ሰው በሕይወት ይኖራል፤ ስሕተት በማድረግ የሚጸና ግን ይሞታል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios