Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘዳግም 11:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ከዚህ በፊት ያላወቃችኋቸውን ባዕዳን አማልክት ወደ መከተል አዘንብላችሁ እነዚህን ትእዛዞች ባትፈጽሙ ግን ርግማን ይመጣባችኋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 መርገሙ ደግሞ፣ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዞች የማትፈጽሙ፣ የማታውቋቸውንም ሌሎች አማልክት ለመከተል እኔ ከማዝዛችሁ መንገድ የምትወጡ ከሆነ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 መርገሙ ደግሞ፥ የጌታ የአምላካችሁን ትእዛዞች የማትፈጽሙ፥ የማታውቋቸውንም ሌሎች አማልክት ለመከተል እኔ ከማዛችሁ መንገድ የምትወጡ ከሆነ ነው።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 መር​ገ​ምም፥ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ባት​ሰሙ፥ ዛሬ ካዘ​ዝ​ኋ​ችሁ መን​ገድ ፈቀቅ ብትሉ፥ ሌሎ​ች​ንም የማ​ታ​ው​ቁ​አ​ቸ​ውን አማ​ል​ክት ብት​ከ​ተሉ፥ ብታ​መ​ል​ኳ​ቸ​ውም ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 መርገምም፥ የአምላካችሁን የእግዚአብሕርን ትእዛዝ ባትሰሙ፥ ዛሬ ካዘዝኋችሁ መንገድ ፈቀቅ ብትሉ፥ ሌሎችንም የማታውቍቸውን አማልክት ብትከተሉ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 11:28
10 Referencias Cruzadas  

“በሕግ መጽሐፍ በተጻፉት ትእዛዞች ሁሉ ጸንቶ የማይኖርና የማይፈጽማቸው ሁሉ የተረገመ ነው” ተብሎ ስለ ተጻፈ “ሕግን በመፈጸም እንጸድቃለን” የሚሉ ሁሉ የተረገሙ ናቸው።


ከዚህ በኋላ በግራው በኩል ያሉትንም እንዲህ ይላቸዋል፤ ‘እናንተ የተረገማችሁ! ከእኔ ወዲያ ራቁ! ለዲያብሎስና ለተከታዮቹ መላእክት ወደ ተዘጋጀው ወደ ዘለዓለም እሳት ሂዱ!


ምንም ነገር ስለማይሳካላቸውና የክፉ ተግባራቸውን ዋጋ ስለሚያገኙ ለክፉዎች ወዮላቸው!


እምቢ ብትሉኝና ብታምፁ ግን ሰይፍ ይበላችኋል፤ ይህን የተናገርኩ እኔ ራሴ እግዚአብሔር ነኝ።”


እግዚአብሔር በክፉ ሰዎች ቤት እርግማንን ያመጣል፤ የደጋግ ሰዎችን ቤት ግን ይባርካል።


መጻተኞችን፥ እናትና አባት የሞቱባቸውን ልጆችና፥ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች በመጨቈን አትበዝብዙ፤ በዚህች ምድር የሚኖሩ ንጹሓን የሆኑ ሰዎችን በግፍ አትግደሉ፤ እንዳትጠፉም ለሐሰተኞች አማልክት አትስገዱ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios