Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዳንኤል 4:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 የዚህ ዛፍ ቅጠሎች ልምላሜ የሚያምር ነበር፤ ሁሉንም ሕዝብ ለመመገብ የሚበቃ ብዙ ፍሬ ነበረው፤ አራዊት በጥላው ሥር መጠለያ አግኝተው፥ ወፎችም በቅርንጫፎቹ ላይ ጎጆአቸውን ሠርተው ይኖሩ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ቅጠሎቹ የሚያምሩ፣ ፍሬውም ተንዠርግጎ ለሁሉ ምግብ የሆነው፣ የዱር አራዊት መጠለያ የሆነውና በቅርንጫፎቹ ላይ ለሰማይ ወፎች ጐጆ መሥሪያ ያለው፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ቅጠሉም አምሮ የነበረው፥ ፍሬውም የበዛው፥ ለሁሉም መብል የነበረበት፥ በበታቹም የምድር አራዊት የተቀመጡ፥ በቅርንጫፎቹም የሰማይ ወፎች ያደሩበት ያየኸው ዛፍ፥

Ver Capítulo Copiar




ዳንኤል 4:21
8 Referencias Cruzadas  

በላያቸውም ወፎች ጎጆዎቻቸውን ይሠራሉ፤ ሸመላዎችም በእነዚያ ዛፎች ላይ መኖሪያቸውን ያበጃሉ።


የምተክለው በእስራኤል በሚገኝ በከፍተኛ ተራራ ላይ ነው፤ ይህንንም የማደርገው ቅርንጫፎችን አስገኝቶ ፍሬ በማፍራት የተዋበ የሊባኖስ ዛፍ እንዲሆን ነው። በሥሩም የተለያዩ ወፎች ይኖሩበታል፤ በቅርንጫፎቹም ጥላ ሥር ክንፍ ያላቸው ፍጥረቶች ሁሉ ጎጆዎቻቸውን ይሠሩበታል።


የወፍ ዐይነቶች ሁሉ በቅርንጫፎቹ ላይ ጎጆአቸውን ሠሩ፤ የምድር አራዊትም ግልገሎቻቸውን በጥላዎቹ ሥር ወለዱ፤ ታላላቅ ሕዝቦች ሁሉ በጥላው ሥር ያርፉ ነበር።


በምድር ሁሉ ላይ ገዢ አድርጎሃል፤ በሰው፥ በእንስሶችና በወፎች ላይ ሥልጣን ሰጥቶሃል፤ ስለዚህ የወርቁ ራስ አንተ ነህ።


ይህም ዛፍ ጫፉ ወደ ሰማይ እስከሚደርስና በዓለም ዙሪያ ያሉ ሰዎች ሁሉ ሊያዩት እስከሚችሉ ድረስ አደገ ጠነከረም።


እነሆ፥ ጫፉ እስከ ሰማይ የደረሰና በዓለም ዙሪያ ላሉት ሰዎች ሁሉ የሚታይ አንድ ትልቅ ዛፍ በራእይ ተመልክተሃል፤


“ንጉሥ ሆይ! ረጅምና ብርቱ የሆነው ያ ዛፍ አንተ ነህ፤ ታላቅነትህ እስከ ሰማይ ከፍ ከፍ ብሎአል፤ ሥልጣንህም በዓለም ሁሉ ላይ ተንሰራፍቶአል።


አንድ ሰው በአትክልቱ ውስጥ የዘራትን የሰናፍጭ ዘር ትመስላለች፤ እርስዋ አድጋ ዛፍ ሆነች፤ ወፎችም በቅርንጫፎችዋ ላይ ጎጆአቸውን ሠሩ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos