Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዳንኤል 11:44 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

44 ከዚያን በኋላ ከምሥራቅና ከሰሜን የሚመጣው ወሬ ያስደነግጠዋል፤ በታላቅ ቊጣ ተነሣሥቶ ብዙ ሰዎችን በማጥፋት እንዳልነበሩ ያደርጋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

44 ነገር ግን ከምሥራቅና ከሰሜን የሚመጣ ወሬ ያስደነግጠዋል፤ ብዙዎችንም ለማጥፋትና ለመደምሰስ በታላቅ ቍጣ ይወጣል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

44 ከምሥራቅና ከሰሜን ግን ወሬ ያውከዋል፥ ብዙ ሰዎችንም ይገድል ዘንድና ፈጽሞ ያጠፋ ዘንድ በታላቅ ቍጣ ይወጣል።

Ver Capítulo Copiar




ዳንኤል 11:44
8 Referencias Cruzadas  

እነዚህ ዐሥር ነገሥታት አንድ ሐሳብ አላቸው፤ እነርሱ ኀይላቸውንና ሥልጣናቸውን ለአውሬው ያስረክባሉ፤


ስድስተኛው መልአክ ጽዋውን በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ ላይ አፈሰሰ፤ ከምሥራቅ ለሚመጡ ነገሥታት መንገድ ለማዘጋጀት የወንዙ ውሃ ደረቀ።


ሮማውያን በመርከብ መጥተው ስለሚወጉት በብርቱ ይደነግጣል፤ ወደ ኋላውም አፈግፍጎ በታላቅ ቊጣ ለአይሁድ የተሰጠውን የተቀደሰ ቃል ኪዳን ያረክሳል፤ ተመልሶም ሃይማኖታቸውን ከካዱት ሰዎች ጋር ይወዳጃል።


በዚያን ጊዜ የግብጽ ንጉሥ እጅግ ተቈጥቶ የሶርያን ንጉሥ ለመውጋት ይነሣሉ፤ የሶርያ ንጉሥ ያሰለፈውንም ታላቅ ሠራዊት ያሸንፋል።


የግብጽን ወርቅ፤ ብርና ሌላውንም የከበረ ነገር ሁሉ ከተደበቀበት ቦታ ይወስዳል፤ ሊቢያንና ኢትዮጵያንም ድል ያደርጋል፤


በባሕሩና ቤተ መቅደሱ በተሠራበት ውብ ኮረብታ መካከል ባለው ስፍራ ታላላቅ ንጉሣዊ ድንኳኖችን ይተክላል፤ ይህም ሁሉ ሆኖ በመጨረሻው ራሱ ይጠፋል፤ የሚረዳውም አያገኝም።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios