Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዳንኤል 1:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ከተመረጡትም መካከል ነገዳቸው ከይሁዳ ወገን የሆነ ዳንኤል፥ ሐናንያ፥ ሚሳኤልና ዐዛርያ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ከእነዚህም መካከል ከይሁዳ የመጡት ዳንኤል፣ አናንያ፣ ሚሳኤልና አዛርያ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 በእነዚህም መካከል ከይሁዳ ልጆች ዳንኤልና አናንያ ሚሳኤልና አዛርያ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar




ዳንኤል 1:6
10 Referencias Cruzadas  

እነዚያ ሦስት ሰዎች ማለትም ኖኅ፥ ዳንኤልና ኢዮብ በውስጥዋ ቢገኙ እንኳ በደግነታቸው ማትረፍ የሚችሉት የራሳቸውን ሕይወት ብቻ ነው፤ ይህን የተናገረ ጌታ እግዚአብሔር ነው።


ስለዚህ እኔ እግዚአብሔር ሕያው አምላክ እንደ መሆኔ ኖኅ፥ ዳንኤልና ኢዮብ እንኳ በዚያ ቢኖሩ በጽድቃቸው የራሳቸውን ሕይወት ብቻ ያድናሉ እንጂ የገዛ ልጆቻቸውን እንኳ ማዳን አይችሉም”፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ከዳንኤል ይበልጥ ጥበበኛ የሆንክ ይመስልሃል፤ ምንም ምሥጢር እንደማይሰወርብህም ታስባለህ፤


ንጉሡ ሁሉንም ባነጋገራቸው ጊዜ ከእነርሱ መካከል ዳንኤልን፥ ሐናንያን፥ ሚሳኤልንና ዐዛርያን የሚወዳደር አልተገኘም፤ ስለዚህ እነርሱ በንጉሡ ፊት እንዲያገለግሉ ተመረጡ።


ከዚህ በኋላ ዳንኤል ወደ ቤቱ ሄደና የሆነውን ነገር ለጓደኞቹ ለሐናንያ፥ ለሚሳኤልና ለዐዛርያ ነገራቸው።


አርዮክ ወዲያውኑ ዳንኤልን ወደ ንጉሥ ናቡከደነፆር ፊት አቀረበውና፥ “ንጉሥ ሆይ! የሕልምህን ትርጒም የሚነግርህ ከይሁዳ ምርኮኞች መካከል አንድ ሰው አግኝቼአለሁ” ሲል ለንጉሡ ተናገረ።


በዚያኑ ጊዜ ዳንኤል በንጉሡ ፊት ቀረበ፤ ንጉሡም እንዲህ አለው፦ “አባቴ ንጉሥ ናቡከደነፆር ማርኮ ካመጣቸው ከይሁዳ ስደተኞች መካከል አንዱ የሆንክ ዳንኤል አንተ ነህን?


ንጉሡም ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ አዘነ፤ ዳንኤልንም ለማዳን ወሰነ፤ ፀሐይም እስክትጠልቅ ድረስ እርሱን ለማዳን የሚችልበትን ዘዴ ሁሉ ለማግኘት ሞከረ።


“ነቢዩ ዳንኤል በተናገረው መሠረት የሚያረክሰውን አጸያፊ ነገር በተቀደሰ ስፍራ ቆሞ ባያችሁ ጊዜ አንባቢው ያስተውል!


“ደግሞ መገኘት በማይገባው ስፍራ የሚያረክሰውን አጸያፊ ነገር ታያላችሁ፤ ይህንንም አንባቢው ያስተውል፤ በዚያን ጊዜ በይሁዳ ምድር ያሉ ወደ ተራራዎች ይሽሹ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos