Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 9:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 የግሪክ ቋንቋ ተናጋሪ ከሆኑት አይሁድ ጋር እየተናገረ ይከራከር ነበር፤ እነርሱ ግን ሊገድሉት ዐቅደው ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ከግሪክ አገር ከመጡት አይሁድ ጋራ እየተነጋገረ ይከራከር ነበር፤ እነርሱ ግን ሊገድሉት ጥረት ያደርጉ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ከግሪክ አገርም መጥተው ከነበሩት አይሁድ ጋር ይነጋገርና ይከራከር ነበር፤ እነርሱ ግን ሊገድሉት ፈለጉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ከግ​ሪክ ሀገር መጥ​ተው የነ​በ​ሩ​ት​ንም አይ​ሁድ ይከ​ራ​ከ​ራ​ቸው ነበር፤ እነ​ር​ሱም ደግሞ ሊገ​ድ​ሉት ፈለጉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ከግሪክ አገርም መጥተው ከነበሩት አይሁድ ጋር ይነጋገርና ይከራከር ነበር፤ እነርሱ ግን ሊገድሉት ፈለጉ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 9:29
13 Referencias Cruzadas  

ይሁን እንጂ ከቆጵሮስና ከቀሬና የመጡ አንዳንድ አማኞች ወደ አንጾኪያ በሄዱ ጊዜ ለግሪኮች ጭምር ስለ ጌታ ኢየሱስ መልካም ዜናን አበሠሩ።


ስለዚህ በምኲራብ ከአይሁድና እግዚአብሔርንም ከሚያመልኩት ሰዎች ጋር በአደባባይም በየቀኑ ከሚያገኛቸው ሰዎች ጋር ይከራከር ነበር።


ወደ ኤፌሶን በደረሱ ጊዜ ጵርስቅላንና አቂላን እዚያ ተዋቸው፤ እርሱ ግን ወደ ምኲራብ ገብቶ ለአይሁድ ንግግር ያደርግ ነበር።


ጳውሎስ ወደ ምኲራብ ሄዶ ለሦስት ወር ያኽል ስለ እግዚአብሔር መንግሥት እየተከራከረና ሕዝቡን እያስረዳ በድፍረት ያስተምር ነበር።


ጌታም ተገልጦልኝ ‘አንተ ስለ እኔ የምትሰጠውን ምስክርነት ስለማይቀበሉ ሳትዘገይ በፍጥነት ከኢየሩሳሌም ውጣ’ አለኝ፤


ከጥቂት ጊዜ በኋላ የአማኞች ቊጥር እየበዛ ሲሄድ የግሪክ ቋንቋ የሚናገሩ አይሁድ የይሁዳ አገር ተወላጆች በሆኑት አይሁድ ላይ ማጒረምረም ጀመሩ፤ ያጒረመረሙትም በየቀኑ ይታደል በነበረው ርዳታ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች ችላ ይሉባቸው ስለ ነበር ነው።


በርናባስ ግን ሳውልን ወደ ሐዋርያት አቀረበውና በመንገድ ሳለ ጌታ እንዴት እንደ ተገለጠለትና እንዳነጋገረው በደማስቆም በኢየሱስ ስም እንዴት በድፍረት እንዳስተማረ ነገራቸው።


ስለዚህ ሳውል ከእነርሱ ጋር ሆኖ በኢየሩሳሌም ይዘዋወር ነበር። በጌታም ስም በድፍረት ያስተምር ነበር፤


በጒዞዬ ብዛት የወንዝና የጐርፍ፥ የሽፍቶችም አደጋ ደርሶብኛል፤ ከአይሁድ ወገኖቼና ከአሕዛብ አደጋ ደርሶብኛል፤ በከተማና በበረሓ በባሕርም አደጋ ደርሶብኛል፤ እንዲሁም ከሐሰተኞች አማኞች አደጋ ደርሶብኛል።


ወዳጆች ሆይ! ስለ ጋራ መዳናችን ልጽፍላችሁ በብርቱ ፈልጌ ነበር፤ አሁን ግን በማያዳግም ሁኔታ እግዚአብሔር ለሕዝቡ አንድ ጊዜ ስለ ሰጠው እምነት በብርቱ እንድትጋደሉ ለመምከር ልጽፍላችሁ ግድ ሆነብኝ።


የመላእክት አለቃ ሚካኤል እንኳ ስለ ሙሴ አስከሬን ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ “ጌታ ይገሥጽህ” አለው እንጂ የስድብ ቃል አልተናገረም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos