Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 8:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ስምዖን እንኳን ሳይቀር አምኖ ተጠመቀና ከፊልጶስ ጋር ተባባሪ ሆነ፤ የሚደረጉትንም ድንቅ ነገሮችና ታላላቅ ተአምራት በማየቱ ይገረም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ራሱ ሲሞን እንኳ ሳይቀር አምኖ ተጠመቀ፤ ፊልጶስንም ተከትሎ ሄደ፤ የሚደረገውን ምልክትና ታላቅ ታምራት አይቶም ተገረመ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ሲሞንም ደግሞ ራሱ አመነ፤ ተጠምቆም ከፊልጶስ ጋር ይተባበር ነበር፤ የሚደረገውንም ምልክትና ታላቅ ተአምራት ባየ ጊዜ ተገረመ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ሲሞ​ንም ወዲ​ያ​ውኑ አምኖ ተጠ​መቀ፤ ፊል​ጶ​ስ​ንም ይከ​ተል ጀመር፤ በፊ​ል​ጶ​ስም እጅ የሚ​ደ​ረ​ገ​ውን ተአ​ም​ርና ታላቅ ኀይል ባየ ጊዜ ይደ​ነቅ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ሲሞንም ደግሞ ራሱ አመነ፤ ተጠምቆም ከፊልጶስ ጋር ይተባበር ነበር፤ የሚደረገውንም ምልክትና ታላቅ ተአምራት ባየ ጊዜ ተገረመ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 8:13
16 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር በጣም አስደናቂ የሆኑ ተአምራትን በጳውሎስ እጅ ያደርግ ነበር።


አብ ወልድን ስለሚወድ የሚሠራውን ሁሉ ያሳየዋል፤ እናንተም እንድትደነቁ ከዚህ የበለጠ ሥራም ያሳየዋል።


በሚቀጥለው ሰንበት ከከተማው ነዋሪዎች አብዛኞቻቸው የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማት ተሰበሰቡ፤


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እኔ አንድ ሥራ ሠራሁ፤ እናንተም ሁላችሁ በዚህ ሥራ ትደነቃላችሁ።


በጭንጫማ መሬት ላይ የወደቀውም ዘር የሚያመለክተው ቃሉን ሰምተው በደስታ የሚቀበሉትን ሰዎች ነው፤ ነገር ግን እነርሱ የሚያምኑት ለጊዜው ነው፤ ሥር ስለሌላቸውም በፈተና ጊዜ ወዲያውኑ ይክዳሉ።


በእኔ የሚያምኑ ሁሉ እነዚህን ተአምራት ያደርጋሉ፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤ በአዲስ ቋንቋም ይናገራሉ፤


ልብህ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ስላልሆነ አንተ ከዚህ ነገር ክፍል ወይም ዕጣ የለህም።


“ውብ በር” እየተባለ በሚጠራው በቤተ መቅደሱ በር አጠገብ ተቀምጦ ምጽዋት ይለምን የነበረው እርሱ መሆኑን ዐወቁ፤ በእርሱ ላይም በተደረገው ነገር ይገረሙና ይደነቁ ጀመር።


ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንዲህ አለ፦ “በዙሪያችሁ ያሉትን ሕዝቦች እስቲ ተመልከቱ፤ በምታዩት ሁሉ እጅግ ተደነቁ፤ ማንም ሰው ቢነግራችሁ እንኳ ልታምኑ የማትችሉትን አስደናቂ ነገር በዘመናችሁ እሠራለሁ።


ኃጢአታቸውንም እየተናዘዙ፥ በዮርዳኖስ ወንዝ በዮሐንስ እጅ ይጠመቁ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios