Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 7:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 “ሙሴ አርባ ዓመት በሞላው ጊዜ ወንድሞቹን የእስራኤልን ልጆች ለመጐብኘት ተነሣሣ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 “ሙሴ አርባ ዓመት በሆነው ጊዜ፣ ወንድሞቹን የእስራኤልን ልጆች ሊጐበኝ በልቡ ዐሰበ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 “ነገር ግን አርባ ዓመት ሲሞላው ወንድሞቹን የእስራኤልን ልጆች ይጐበኝ ዘንድ በልቡ አሰበ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 “አርባ ዓመት ሲሞ​ላ​ውም ወን​ድ​ሞ​ቹን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ሊጐ​በ​ኛ​ቸው በልቡ ዐሰበ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ነገር ግን አርባ ዓመት ሲሞላው ወንድሞቹን የእስራኤልን ልጆች ይጐበኝ ዘንድ በልቡ አሰበ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 7:23
18 Referencias Cruzadas  

ደግሞም አንድ ልብ ይሰጣቸው ዘንድ፥ በእግዚአብሔር ቃል የሆነውን የንጉሡንና የባለሥልጣኖቹን ትእዛዝ ያደርጉ ዘንድ እግዚአብሔር የይሁዳን ሕዝብ ልብ አነሣሣ።


እግዚአብሔር በነቢዩ ኤርምያስ አማካይነት አስቀድሞ የተናገረውን የትንቢት ቃል የፋርስ ተወላጅ ቂሮስ ንጉሠ ነገሥት በሆነ በመጀመሪያው ዓመት ፈጸመው፤ ይኸውም እግዚአብሔር ራሱ ቂሮስን አነሣሥቶ ከዚህ የሚከተለውን ትእዛዝ በጽሑፍ በማወጅ በንጉሠ ነገሥት ግዛቱ ሁሉ እንዲነበብ አደረገ።


ከዚያም በኋላ የይሁዳና የብንያም ነገዶች የቤተሰብ አለቆች፥ ካህናትና ሌዋውያን፥ እንዲሁም እግዚአብሔር ልቡን ያነሣሣው ሌላውም ሰው ሁሉ፥ ተመልሶ ለመሄድና በኢየሩሳሌም የሚገኘውን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ እንደገና ለመሥራት ተዘጋጀ።


ዕዝራ እንዲህ ሲል እግዚአብሔርን አመሰገነ፦ “የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን! በኢየሩሳሌም ለሚሠራው ለእግዚአብሔር ቤት ንጉሠ ነገሥቱ ክብር ለመስጠት እንዲፈቅድ ያደረገው እርሱ ነው፤


ለመሥራት እያንዳንዱ ለመስጠት ልቡ የፈቀደውን ለእግዚአብሔር መባ አመጣ፤ በዚህም ዐይነት እስራኤላውያን ለመንፈሳዊ አገልግሎት ለካህናት ልብስ የሚሆነውን ነገር ሁሉ አመጡ።


ወንዶችና ሴቶች የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ እግዚአብሔር ሙሴን ላዘዘው ሥራ የሚውል ልባቸው የፈቀደውን ስጦታ ለእግዚአብሔር አመጡ።


ሙሴም ወደ ዐማቱ ወደ የትሮ ተመልሶ ሄደና “በግብጽ ወደሚኖሩት ወገኖቼ ተመልሼ ሄጄ በሕይወት መኖራቸውን እንዳይ ፍቀድልኝ” አለው። የትሮም ፈቅዶ “በሰላም ሂድ” አለው።


ከንጉሡም ጋር በተነጋገሩበት በዚያ ጊዜ ሙሴ የሰማንያ ዓመት ዕድሜ ሲኖረው፥ አሮን ደግሞ ሰማንያ ሦስት ዓመት ሆኖት ነበር።


የንጉሥ ልብ በእግዚአብሔር እጅ ነው፤ እርሱንም እንደ ወራጅ ውሃ ወደ ፈቀደው ይመራዋል። የንጉሥንም አእምሮ ይቈጣጠራል።


ከጥቂት ቀኖች በኋላ ጳውሎስ በርናባስን “ና እንመለስና ከዚህ በፊት የጌታን ቃል ባበሠርንባቸው ከተሞች ሁሉ ያሉትን ወንድሞች እንጐብኝ፤ እንዴት እንደ ሆኑም እንወቅ” አለው።


ከወንድሞቹም አንዱ በአንድ ግብጻዊ ሰው ሲበደልና ሲገፋ አይቶ ረዳው፤ ለተገፋውም በመበቀል ግብጻዊውን መታና ገደለው።


እኔ ለእናንተ የማስበውን ያኽል ቲቶም ለእናንተ ከልቡ እንዲያስብ ያደረገ አምላክ ይመስገን።


መልካም ስጦታና ፍጹም በረከት ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፤ ይህም የሚመጣው እንደ ጥላ መዘዋወር ወይም መለዋወጥ ከሌለበት ከብርሃን አባት ከእግዚአብሔር ነው።


ዕቅዱን እንዲፈጽሙ ይህን ሐሳብ በልባቸው ያኖረ እግዚአብሔር ነው፤ ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል እስኪፈጸም እነርሱ በአንድ ሐሳብ ይስማማሉ፤ የመንገሥ ሥልጣናቸውንም ለአውሬው ያስረክባሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos