Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 4:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እነርሱም ሁለቱን ሐዋርያት በመካከላቸው አቁመው፥ “ይህን ያደረጋችኹት በምን ኀይል ወይም በማን ስም ነው?” ሲሉ ጠየቁአቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እነርሱም ጴጥሮስንና ዮሐንስን በመካከል አቁመው፣ “ይህን ያደረጋችሁት በምን ኀይል ወይም በማን ስም ነው?” ብለው ጠየቋቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 እነርሱንም በመካከል አቁመው “በምን ኃይል ወይስ በማን ስም እናንተ ይህን አደረጋችሁ?” ብለው ጠየቁአቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 በአ​ደ​ባ​ባ​ይም አቆ​ሙና፥ “እና​ንተ ይህን በማን ስምና በማን ኀይል አደ​ረ​ጋ​ች​ሁት?” ብለው መረ​መ​ሩ​አ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 እነርሱንም በመካከል አቁመው፦ “በምን ኃይል ወይስ በማን ስም እናንተ ይህን አደረጋችሁ?” ብለው ጠየቁአቸው።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 4:7
12 Referencias Cruzadas  

ሰውየውም “አንተን በእኛ ላይ ገዢና ዳኛ አድርጎ የሾመህ ማን ነው? ወይስ ያንን ግብጻዊ እንደ ገደልክ እኔንም መግደል ትፈልጋለህን?” አለው፤ ሙሴም እጅግ ፈርቶ “ያደረግኹት ነገር ታውቋል ማለት ነው” ብሎ አሰበ።


ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ ያስተምር ነበር። በዚያን ጊዜ የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሽማግሌዎች ወደ እርሱ ቀረቡና “ይህን ሁሉ የምታደርገው በምን ሥልጣን ነው? ይህን ሥልጣን የሰጠህስ ማን ነው?” ሲሉ ጠየቁት።


“እነዚህን ነገሮች የምታደርገው በምን ሥልጣን ነው? ወይስ እነዚህን ነገሮች እንድታደርግ ሥልጣን የሰጠህ ማን ነው?” ሲሉ ጠየቁት።


ከዚህ በኋላ የአይሁድ ባለሥልጣኖች ኢየሱስን፦ “አንተ ይህን ለማድረግ ሥልጣን እንዳለህ ምን ተአምር ታሳየናለህ?” አሉት።


የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ስታመነዝር የተያዘች ሴት አመጡና በሕዝቡ መካከል አቆሙአት።


እነርሱም ይህን በሰሙ ጊዜ ከሽማግሌዎች ጀምሮ ሁሉም አንድ በአንድ ከዚያ ሄዱ፤ ስለዚህ ኢየሱስ በመካከል ቆማ ከነበረችው ሴት ጋር ብቻውን ቀረ።


ይህ ሰው ድኖ በፊታችሁ የቆመው እናንተ በሰቀላችሁትና እግዚአብሔር ግን ከሞት ባስነሣው በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንደ ሆነ ለእናንተ ለሁላችሁና ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ የታወቀ ይሁን።


ከተሰበሰቡት ሰዎች መካከል የካህናት አለቃው ሐናና ቀያፋ፥ ዮሐንስና እስክንድሮስ፥ የካህናት አለቃው ቤተሰቦች ሁሉ ይገኙባቸዋል፤


በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እናንተ የሕዝብ አለቆችና ሽማግሌዎች ሆይ!


ከዚህ በኋላ ሐዋርያቱን ወደ እነርሱ ጠርተው አስገረፉአቸው፤ የኢየሱስንም ስም በመጥራት እንዳይናገሩ አዘዙአቸውና ለቀቁአቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos