Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 23:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ነገር ግን የጳውሎስ የእኅት ልጅ ይህን ሤራ ስለ ሰማ ወደ ወታደሮች ሰፈር ሄዶ ገባና ለጳውሎስ ነገረው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ነገር ግን የጳውሎስ የእኅት ልጅ ስለ ሤራው በመስማቱ፣ ወደ ጦሩ ሰፈር ገብቶ ሁኔታውን ለጳውሎስ ነገረው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 የጳውሎስ የእኅቱ ልጅ ግን ደባቸውን በሰማ ጊዜ፥ መጥቶ ወደ ሰፈሩ ገባና ለጳውሎስ ነገረው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 የጳ​ው​ሎ​ስም የእ​ኅቱ ልጅ ምክ​ራ​ቸ​ውን በሰማ ጊዜ ሄዶ ወደ ወታ​ደ​ሮች ሰፈር ገባና ለጳ​ው​ሎስ ነገ​ረው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 የጳውሎስ የእኅቱ ልጅ ግን ደባቸውን በሰማ ጊዜ፥ መጥቶ ወደ ሰፈሩ ገባና ለጳውሎስ ነገረው።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 23:16
12 Referencias Cruzadas  

ጠቡ እየከረረ ስለ ሄደ ሰዎቹ ጳውሎስን እንዳይቦጫጭቁት ፈርቶ አዛዡ “ውረዱና ጳውሎስን ከሰዎቹ መካከል ነጥቃችሁ አምጡ! ወደ ጦሩ ሰፈርም ውሰዱት!” በማለት ወታደሮቹን አዘዘ።


የዚህ ዓለም ጥበብ በእግዚአብሔር ፊት ሞኝነት ነው፤ ይህም፦ “እግዚአብሔር ጥበበኞችን በተንኰላቸው ይይዛቸዋል” ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው።


በማግስቱ ፈረሰኞቹ ከጳውሎስ ጋር ጒዞአቸውን እንዲቀጥሉ አድርገው እነርሱ ወደ ጦር ሰፈሩ ተመለሱ።


ሕዝቡም አንዳንዶቹ አንድ ነገር ሲሉ፥ ሌሎች ሌላ ነገር ይሉ ነበር፤ አዛዡ ከሕዝቡ ጩኸት የተነሣ እርግጠኛውን ነገር ለማወቅ ስላልቻለ ጳውሎስን ወደ ወታደሮቹ ሰፈር እንዲወስዱት አዘዘ።


እግዚአብሔር አስቀድሞ የወሰነው ካልሆነ በትእዛዙ አንድን ነገር ማስደረግ የሚችል ማነው?


ሰው በጥበቡ፥ በአስተዋይነቱና በዕቅዱ በእግዚአብሔር ላይ መነሣት አይችልም።


ጥበበኞችን የራሳቸው ተንኰል ወጥመድ ሆኖ እንዲይዛቸው ያደርጋል የተንኰለኞችም ዕቅድ በፍጥነት ይጠፋል።


የአብያታር ልጅ ዮናታንና የሳዶቅ ልጅ አሒማዓጽ ወደ ከተማይቱ ሲገቡ ማንም እንዳያያቸው ስለ ፈሩ፥ ከኢየሩሳሌም አካባቢ ባለችው በዔንሮጌል ምንጭ አጠገብ ይጠባበቁ ነበር፤ አንዲት ልጃገረድ አገልጋይም ዘወትር ወደዚያ እየሄደች የሚሆነውን ነገር ሁሉ ትነግራቸው ነበር፤ ከዚያም በኋላ እነርሱ ሄደው ለንጉሥ ዳዊት ይነግሩት ነበር።


ወታደሮች ወደ ጦር ሰፈራቸው ሊያስገቡት በቀረቡ ጊዜ ጳውሎስ የጦር አዛዡን “አንድ ነገር እንድነግርህ ትፈቅድልኛለህን?” አለው። አዛዡም “የግሪክ ቋንቋ ታውቃለህን?


ጳውሎስም ከመቶ አለቆች አንዱን ጠርቶ “ይህ ልጅ ለጦር አዛዡ የሚናገረው ነገር ስላለው ወደ እርሱ አቅርበው” አለው።


ጳውሎስን ይጠብቅ የነበረውንም መቶ አለቃ “እምብዛም ነጻነት ሳትከለክለው በጥንቃቄ ጠብቀው፤ ወዳጆቹም የሚያስፈልገውን ሁሉ ይዘውለት ሲመጡ አትከልክልበት” አለው።


እንደ ዐመፀኛ ሰው የጻድቁን ሰው ቤት ለመዝረፍ አትሸምቅ፤ መኖሪያውንም አትውረር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios