Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 21:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 በማግስቱ ከዚያ ወጥተን ወደ ቂሳርያ ሄድን፤ እዚያ ከሰባቱ ዲያቆናት አንዱ ወደ ሆነው ወደ ወንጌላዊው ፊልጶስ ቤት ገባንና ከእርሱ ጋር ተቀመጥን።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 በማግስቱም ከዚያ ተነሥተን ቂሳርያ ደረስን፤ ከሰባቱ ወንጌላውያን አንዱ በሆነው በፊልጶስ ቤትም ዐረፍን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 በነገውም ወጥተን ወደ ቂሣርያ መጣን፤ ከሰባቱም አንድ በሚሆን በወንጌላዊው ፊልጶስ ቤት ገብተን በእርሱ ዘንድ ተቀመጥን።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 በማ​ግ​ሥ​ቱም ወጥ​ተን ወደ ቂሳ​ርያ ሄድን፤ ወደ ወን​ጌ​ላ​ዊው ወደ ፊል​ጶስ ቤትም ገባን፤ እር​ሱም ከሰ​ባቱ ወን​ድ​ሞች ዲያ​ቆ​ናት አንዱ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 በነገውም ወጥተን ወደ ቂሣርያ መጣን፥ ከሰባቱም አንድ በሚሆን በወንጌላዊው ፊልጶስ ቤት ገብተን በእርሱ ዘንድ ተቀመጥን።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 21:8
18 Referencias Cruzadas  

በቂሳርያ የሚኖር ቆርኔሌዎስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም በሮማውያን ጦር ሠራዊት ሥር “የኢጣልያ ብርጌድ” በሚባለው ውስጥ የመቶ አለቃ ነበር።


ጳውሎስ ይህን ራእይ ካየ በኋላ ወዲያውኑ ወደ መቄዶንያ ለመሄድ ፈለግን፤ ይህም የሆነው ለመቄዶንያ ሰዎችም ወንጌልን እንድናስተምር ጌታ እንደ ጠራን ስለ ተረዳን ነው።


በሰንበትም ቀን ለጸሎት ይሰበሰቡበት ወደነበረው ከከተማው ውጪ ወደሚገኘው ወደ ወንዝ ዳር ሄድን፤ እዚያም ተቀምጠን ለተሰበሰቡት ሴቶች የእግዚአብሔርን ቃል አስተማርን።


አንድ ቀን ወደ ጸሎት ቦታ ስንሄድ ወደፊት የሚሆነውን ነገር በጥንቈላ የሚያናግር ርኩስ መንፈስ ያደረባት አንዲት አገልጋይ ልጃገረድ በመንገድ አገኘችን፤ ይህች ልጃገረድ በጥንቈላዋ ለአሳዳሪዎችዋ ብዙ ትርፍ ታስገኝላቸው ነበር።


ወደ ቂሳርያም በደረሰ ጊዜ ከዚያ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ ለቤተ ክርስቲያን ሰዎች ሰላምታ ከሰጠ በኋላ ተመልሶ ወደ አንጾኪያ ወረደ።


ጳውሎስን ለማሳፈር ስለ አሰብን እኛ ቀድመን በመርከብ ወደ አሶስ ሄድን፤ ይህንንም ያደረግነው ጳውሎስ እስከ አሶስ ድረስ በእግሩ ለመሄድ ስለ ወሰነና እንዲህ እንድናደርግ ስለ አዘዘን ነው።


እኛ ግን ከቂጣ በዓል በኋላ ከፊልጵስዩስ በመርከብ ተሳፍረን በአምስት ቀን እነርሱ ወዳሉበት ወደ ጢሮአዳ ደረስንና እዚያ ሰባት ቀን አሳለፍን።


በቂሳርያ የነበሩ አንዳንድ ምእመናን አብረውን መጡ፤ እነርሱም በምናሶን ቤት እንድናርፍ ወደ እርሱ ቤት መሩን፤ ይህ ሰው ቀደም ብሎ ያመነ፥ የቆጵሮስ ተወላጅ ነበር።


ከዚህ በኋላ የጦር አዛዡ ከመቶ አለቆቹ ሁለቱን ጠርቶ “ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ሲሆን ወደ ቂሳርያ የሚሄዱ ሁለት መቶ ወታደሮችና ሰባ ፈረሰኞች፤ ሁለት መቶ ጦር ወርዋሪዎችም አዘጋጁ፤


ወደ ኢጣሊያ በመርከብ እንድንሄድ በተወሰነ ጊዜ ጳውሎስንና ሌሎችንም እስረኞች በአውግስጦስ ክፍለ ጦር ውስጥ ለነበረው ዩልዮስ ለሚባለው መቶ አለቃ አስረከቡአቸው።


ሦስት ወር በማልታ ከቈየን በኋላ ክረምቱን በደሴቲቱ ባሳለፈው በእስክንድርያው መርከብ ተሳፍረን ተነሣን፤ መርከቡ ዲዮስቆሮስ የተባሉ የመንታ አማልክት አርማ ነበረበት።


ወደ ሮም በገባን ጊዜ ጳውሎስ አንድ የሚጠብቀው ወታደር ተሰጠውና ብቻውን እንዲኖር ተፈቀደለት።


ይህ አባባል ሁሉንም አስደሰተ ቀጥሎ ያሉትም ሰዎች ተመረጡ፤ እነርሱም በእምነትና በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ እስጢፋኖስን፥ ፊልጶስ፥ ጵሮኮሮስ፥ ኒቃሮና፥ ጢሞና፥ ጰርሜና የአይሁድን እምነት ተቀብሎ የነበረው የአንጾኪያው ኒቆላዎስ ናቸው።


ወንድሞች ይህን ባወቁ ጊዜ ወደ ቂሣርያ ወሰዱት፤ ከዚያም ወደ ጠርሴስ እንዲሄድ አደረጉ።


እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ አንዳንዶቹ ነቢያት፥ አንዳንዶቹ የወንጌል ሰባኪዎች፥ አንዳንዶቹ የምእመናን እረኞች፥ አንዳንዶቹ አስተማሪዎች እንዲሆኑ ስጦታዎችን ሰጣቸው።


አንተ ግን በሁሉ ነገር ጥንቁቅ ሁን፤ መከራን በመቀበል ጽና፤ የወንጌል ሰባኪነትን ሥራ አከናውን፤ አገልግሎትህንም ሁሉ ፈጽም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos