Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 15:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እግዚአብሔር አንድ በስሙ የሚጠራ ሕዝብን ከመካከላቸው ለመምረጥ ለመጀመሪያ ጊዜ አሕዛብን እንዴት እንደ ጐበኘ ስምዖን አስረድቶአል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እግዚአብሔር ከአሕዛብ ወገን ለርሱ የሚሆነውን ሕዝብ አስቀድሞ እንዴት እንደ ጐበኘ ስምዖን አስረድቶናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 እግዚአብሔር ለስሙ የሚሆንን ወገን ከአሕዛብ ይወስድ ዘንድ አስቀድሞ እንዴት እንደ ጐበኘ ስምዖን ተርኮአል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ስም​ዖ​ንም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አስ​ቀ​ድሞ አሕ​ዛ​ብን ይቅር እን​ዳ​ላ​ቸ​ውና ከው​ስ​ጣ​ቸ​ውም ለስሙ ሕዝ​ብን እንደ መረጠ ተና​ግ​ሮ​አል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እግዚአብሔር ለስሙ የሚሆንን ወገን ከአሕዛብ ይወስድ ዘንድ አስቀድሞ እንዴት እንደ ጐበኘ ስምዖን ተርኮአል።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 15:14
11 Referencias Cruzadas  

የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይና ሐዋርያ ከሆነው ከስምዖን ጴጥሮስ፥ ከአምላካችንና ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ በሚገኘው ጽድቅ አማካይነት እኛ እንዳገኘነው እምነት ያለ የከበረ እምነት ላገኛችሁት፤


እነርሱም ለራሴ የሠራኋቸው ሕዝቦች ስለ ሆኑ እኔን ያመሰግናሉ።”


ስለ ክርስቶስ ስም አሕዛብ ሁሉ እንዲያምኑና እንዲታዘዙ ለማድረግ በእርሱ አማካይነት ለሐዋርያነት የሚያበቃንን ጸጋ ተቀብለናል።


ሁሉም ነገር የተገኘው ከእርሱ፥ በእርሱና ለእርሱ ነው፤ ለዘለዓለም ክብር ለእርሱ ይሁን! አሜን!


አምላካችን መሓሪና ርኅሩኅ በመሆኑ የደኅንነት ብርሃን ከወደላይ እንዲበራልን ያደርጋል።


“ሕዝቡን በምሕረት ስለ ጐበኘና ስላዳነ፥ የእስራኤል አምላክ፥ ጌታ ይመስገን!


በዚያን ጊዜ በኢየሩሳሌም ስምዖን የሚባል አንድ ሰው ነበር፤ እርሱም ሕይወቱን ለእግዚአብሔር የሰጠ ጻድቅ ሰው ነበር፤ የእስራኤልን የመዳን ተስፋ ይጠባበቅ ነበር፤ መንፈስ ቅዱስም በእርሱ ላይ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios