Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 13:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እነርሱ ጌታን ሲያገለግሉና ሲጾሙ ሳሉ መንፈስ ቅዱስ “እኔ ለመረጥኳቸው ሥራ በርናባስንና ሳውልን ለዩልኝ!” አለ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እነዚህም ጌታን እያመለኩና እየጾሙ ሳሉ፣ መንፈስ ቅዱስ፣ “በርናባስንና ሳውልን እኔ ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ” አለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 እነዚህም ጌታን ሲያመልኩና ሲጦሙ መንፈስ ቅዱስ “በርናባስንና ሳውልን ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ፤” አለ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ሲሠሩ፥ ሲጾ​ሙም መን​ፈስ ቅዱስ፥ “በር​ና​ባ​ስ​ንና ሳው​ልን እኔ ለፈ​ለ​ግ​ኋ​ቸው ሥራ ለዩ​ልኝ” አላ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 እነዚህም ጌታን ሲያመልኩና ሲጦሙ መንፈስ ቅዱስ፦ “በርናባስንና ሳውልን ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ” አለ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 13:2
41 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን ከመወለዴ በፊት እግዚአብሔር መረጠኝ፤ በጸጋውም ጠራኝ።


ጌታም ሐናንያን እንዲህ አለው፦ “እርሱ ስሜን ለአረማውያን፥ ለነገሥታትና ለእስራኤል ሰዎች የሚያሳውቅ፥ የእኔ ምርጥ መሣሪያ ስለ ሆነ ወደ እርሱ ሂድ፤


እኔም የዚህ ወንጌል አብሣሪ፥ ሐዋርያ፥ አስተማሪ ሆኜ ተሾሜአለሁ።


ይሁን እንጂ ይህን ሁሉ የሚያደርገው ያው አንዱ መንፈስ ቅዱስ ነው፤ መንፈስ ቅዱስ እንደ ፈቀደ ለእያንዳንዱ ሰው የተለየ ስጦታን ይሰጠዋል።


የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ከሆነው፥ ለሐዋርያነት ከተጠራው፥ የእግዚአብሔርንም ወንጌል ለማስተማር ከተመረጠው ከጳውሎስ የተላከ።


እኔም እምነትንና እውነትን ለማብሠር ሐዋርያና አስተማሪ ሆኜ ወደ አሕዛብ የተላክሁት በዚህ ምክንያት ነው፤ ይህንንም ስል እውነት እናገራለሁ እንጂ አልዋሽም።


ጌታም ‘በሩቅ ወዳሉ ወደ አሕዛብ ስለምልክህ ተነሥና ሂድ!’ አለኝ።”


ከዚያም ስለ ፈጸሙት ሥራ ለእግዚአብሔር ጸጋ ዐደራ ወደ ተሰጡበት ወደ አንጾኪያ በመርከብ ሄዱ።


ማቅ ለብሼና ዐመድ ላይ ተቀምጬ በመጾም ጸሎቴንና ልመናዬን ለማቅረብ ፊቴን ወደ ጌታ እግዚአብሔር መለስኩ።


ለአርኪጳስም “በጌታ አገልግሎት የተሰጠህን ሥራ በጥንቃቄ እንድትፈጽም” ብላችሁ ንገሩልኝ።


ከዚህም በኋላ ዕድሜዋ ሰማኒያ አራት ዓመት እስኪሆን ድረስ ከቤተ መቅደስ ሳትለይ በጾምና በጸሎት ቀንና ሌሊት እግዚአብሔርን ታገለግል ነበር።


ከዚህ በኋላ ሕልቃና በራማ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ተመልሶ ሄደ፤ ሕፃኑ ሳሙኤልም በካህኑ ዔሊ ሥር ሆኖ እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር።


በብዙ ምስክሮች ፊት ከእኔ የተማርከውን ትምህርት ሌሎችን ለማስተማር ችሎታ ላላቸውና ለታመኑ ሰዎች ዐደራ ስጥ።


እግዚአብሔር በኀይሉ አሠራር በሰጠኝ የጸጋ ስጦታ እኔም የዚህ ወንጌል አገልጋይ ሆኜአለሁ።


እነርሱም ጾመውና ጸልየው እጆቻቸውን ከጫኑባቸው በኋላ ላኳቸው።


ቆርኔሌዎስም እንዲህ አለ፦ “ከአራት ቀን በፊት ልክ በዚህ ጊዜ በዘጠኝ ሰዓት በቤቴ እጸልይ ነበር፤ እነሆ፥ በድንገት አንድ የሚያንጸባርቅ ልብስ የለበሰ ሰው በፊቴ ቆመ፤


ጴጥሮስ የራእዩን ነገር በማሰላሰል ላይ ሳለ መንፈስ ቅዱስ እንዲህ አለው፦ “እነሆ! ሦስት ሰዎች ይፈልጉሃል፤


በዚህ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ፊልጶስን “ሂድ ወደዚያ ሠረገላ ቅረብና ተገናኘው” አለው።


እንግዲህ ሠራተኞችን ወደ መከሩ ሥራ እንዲልክ የመከሩን ጌታ ለምኑት።”


ኢየሱስም ቀጥሎ እንዲህ አለ፦ “በምትጾሙበት ጊዜ፥ መጾማቸውን ሰዎች እንዲያውቁላቸው፥ ፊታቸውን እንደሚለውጡት እንደ ግብዞች፥ ፊታችሁን አታጠውልጉ፤ በእውነት እላችኋለሁ፥ እነርሱ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።


በዚያን ጊዜ፥ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት እንዲሸከሙ፥ በፊቱም በመቆም እንዲያገለግሉትና ሕዝቡን በእግዚአብሔር ስም እንዲባርኩ የሌዊን ነገድ በመለየት ሾመ፤ እስከ ዛሬም ድረስ የሌዊ ነገድ ትውልድ አገልግሎት ይኸው ነው።


እንደ አሮን በእግዚአብሔር የተጠራ ካልሆነ በቀር ማንም ይህን ክብር በገዛ ራሱ አያገኝም።


ከእኔ ጋር ያለው ሉቃስ ብቻ ነው፤ ማርቆስ ለአገልግሎት ስለሚጠቅመኝ ፈልገህ ይዘኸው ና።


አንተ ግን በሁሉ ነገር ጥንቁቅ ሁን፤ መከራን በመቀበል ጽና፤ የወንጌል ሰባኪነትን ሥራ አከናውን፤ አገልግሎትህንም ሁሉ ፈጽም።


ብዙ ሥራና ድካም ነበረብኝ፤ ብዙ ጊዜ እንቅልፍ አጥቻለሁ፤ በራብና በውሃ ጥም ተጨንቄአለሁ፤ ብዙ ጊዜም የምግብ እጦት ደርሶብኛል፤ ብርድና መራቆትም ደርሶብኛል።


የእግዚአብሔር አገልጋዮች መሆናችንን የምንገልጠውም በመገረፍ፥ በመታሰር፥ በመታወክ፥ በሥራ በመድከም፥ እንቅልፍ በማጣትና በመራብ ነው፤


በጸሎት ለመትጋት ሁለታችሁም ተስማምታችሁ ለተወሰነ ጊዜ ካልሆነ በቀር በመለያየት አንዱ የሌላውን የጋብቻ መብት አይከልክል። በዚህም ምክንያት ራሳችሁን መቈጣጠር አቅቶአችሁ ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ እንደገና አብራችሁ ሁኑ።


ይህም ጸጋ የተሰጠኝ የእግዚአብሔርን የምሥራች ቃል ለአሕዛብ በማብሠር እንደ ካህን ሆኜ ኢየሱስ ክርስቶስን ለማገልገል ነው፤ ስለዚህ አሕዛብ በመንፈስ ቅዱስ የተቀደሰና እግዚአብሔርንም ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ አገለግላለሁ።


አስተማሪዎች ካልተላኩስ እንዴት ቃሉን ሊያስተምሩ ይችላሉ? ይህም “የመልካም ዜና አብሣሪዎች መምጣት እንዴት ደስ ያሰኛል!” ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው።


መንፈስ ቅዱስ እናንተን ኤጲስ ቆጶሳት አድርጎ ሾሞአችኋል፤ እንግዲህ ለራሳችሁና ለመንጋው ተጠንቀቁ፤ እግዚአብሔር በገዛ ልጁ ደም የዋጃትን ቤተ ክርስቲያን ጠብቁ።


እኛ ግን በመጸለይና የእግዚአብሔርን ቃል በማስተማር እንተጋለን።”


በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ለፊት ሆነው ምስጋና፥ ውዳሴና ክብር በማቅረብ ለእግዚአብሔር አምላክ የሚደረገውን የአምልኮ ሥነ ሥርዓት እንዲመሩ ዳዊት ጥቂት ሌዋውያንን ሾመ።


ከዚህ በኋላ ጌታ፥ ሌሎች ሰባ ሁለት ሰዎችን መረጠ፤ እርሱ ሊሄድበት ወደአሰበውም ከተማና ቦታ ሁሉ ቀድመውት እንዲሄዱ ሁለት ሁለት አድርጎ ላካቸው።


የቆጵሮስ ተወላጅ የሆነ፥ ዮሴፍ የሚባል አንድ ሌዋዊ ነበረ፤ ሐዋርያት “በርናባስ” እያሉ ይጠሩት ነበር፤ ትርጓሜው “የመጽናናት ልጅ” ማለት ነው።


በርናባስና ሳውል በመንፈስ ቅዱስ ተልከው ወደ ሴሌውቅያ ሄዱ፤ ከዚያም በመርከብ ወደ ቆጵሮስ ተጓዙ።


እንዲህ ዐይነቱ ጋኔን ግን በጸሎትና በጾም ካልሆነ በቀር ከቶ አይወጣም።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios