Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 12:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ይህን ካረጋገጠ በኋላ ብዙ ሰዎች በአንድነት ተሰብስበው ወደሚጸልዩበት ወደ ማርያም ቤት ሄደ፤ ይህችም ማርያም ማርቆስ የተባለው የዮሐንስ እናት ነበረች።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ይህን ከተረዳ በኋላም፣ ብዙ ሰዎች ተሰብስበው በአንድነት ወደሚጸልዩበት፣ ማርቆስ ወደተባለው ወደ ዮሐንስ እናት ወደ ማርያም ቤት ሄደ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ባስተዋለም ጊዜ እጅግ ሰዎች ተከማችተው ይጸልዩበት ወደነበረው ማርቆስ ወደ ተባለው ወደ ዮሐንስ እናት ወደ ማርያም ቤት መጣ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ከዚ​ህም በኋላ በአ​ስ​ተ​ዋለ ጊዜ ብዙ​ዎች ወን​ድ​ሞች ተሰ​ብ​ስ​በው ይጸ​ል​ዩ​በት ወደ ነበ​ረው ማር​ቆስ ወደ​ተ​ባ​ለው ወደ ዮሐ​ንስ እናት ወደ ማር​ያም ቤት ሄደ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ባስተዋለም ጊዜ እጅግ ሰዎች ተከማችተው ይጸልዩበት ወደ ነበረው ማርቆስ ወደ ተባለው ወደ ዮሐንስ እናት ወደ ማርያም ቤት መጣ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 12:12
14 Referencias Cruzadas  

እኔን በልመና ከመጥራታቸው በፊት እመልስላቸዋለሁ፤ እየጸለዩም ሳለ እሰማቸዋለሁ።


በርናባስና ሳውል አገልግሎታቸውን ፈጽመው ከኢየሩሳሌም ወደ አንጾኪያ ተመለሱ፤ ማርቆስ የተባለውን ዮሐንስንም ከእነርሱ ጋር ይዘውት መጡ።


ስለዚህ ጴጥሮስ በወህኒ ቤት ተይዞ ይጠበቅ ነበር፤ ነገር ግን ቤተ ክርስቲያን ስለ እርሱ ወደ እግዚአብሔር በጥብቅ ትጸልይ ነበር።


ከዚህ በኋላ ጳውሎስና ጓደኞቹ በመርከብ ተሳፍረው ከጳፉ በጵንፍልያ ወደምትገኘው ወደ ጴርጌ ሄዱ፤ ማርቆስ የተባለው ዮሐንስ ግን ከእነርሱ ተለይቶ ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሶ ሄደ።


ወደ ሰላሚስ ከተማ በደረሱ ጊዜ በአይሁድ ምኲራቦች የእግዚአብሔርን ቃል አስተማሩ፤ ዮሐንስ ማርቆስም ከእነርሱ ጋር ሆኖ ይረዳቸው ነበር።


ጳውሎስና ሲላስም ከወህኒ ቤት ወጥተው ወደ ልድያ ቤት ገቡ፤ እዚያም ወንድሞችን አግኝተው፥ አጽናኑአቸውና ከተማውን ለቀው ሄዱ።


ጴጥሮስና ዮሐንስ ተለቀው ወደ ጓደኞቻቸው በተመለሱ ጊዜ የካህናት አለቆችና የአይሁድ ሽማግሌዎች ያሉአቸውን ሁሉ ነገሩአቸው።


ከእኔ ጋር የታሰረው አርስጥሮኮስም ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ አንድ ጊዜ፥ “ወደ እናንተ በሚመጣበት ጊዜ እንድትቀበሉት” ብዬ አሳስቤአችሁ የነበረው የበርናባስ የአጐቱ ልጅ ማርቆስም ሰላምታ ያቀርብላችኋል።


ከእኔ ጋር ያለው ሉቃስ ብቻ ነው፤ ማርቆስ ለአገልግሎት ስለሚጠቅመኝ ፈልገህ ይዘኸው ና።


እንዲሁም የሥራ ጓደኞቼ የሆኑት ማርቆስ፥ አርስጥሮኮስ፥ ዴማስና፥ ሉቃስ ሰላምታ ያቀርቡልሃል።


እንደ እናንተ የተመረጠችው፥ በባቢሎን ያለችው እኅት ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ ታቀርብላችኋለች፤ ልጄ ማርቆስም ሰላምታ ያቀርብላችኋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos