Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 11:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ስለዚህ በአንጾኪያ የሚኖሩ ምእመናን በይሁዳ ለሚኖሩ ወንድሞች እያንዳንዳቸው እንደየችሎታቸው በማዋጣት ርዳታ እንዲላክ ወሰኑ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ደቀ መዛሙርትም እያንዳንዳቸው ዐቅማቸው በፈቀደ መጠን አዋጥተው በይሁዳ የሚኖሩትን ወንድሞች ለመርዳት ወሰኑ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ደቀ መዛሙርትም እያንዳንዳቸው እንደ ችሎታቸው መጠን አዋጥተው በይሁዳ ለሚኖሩት ወንድሞች እርዳታን ይልኩ ዘንድ ወሰኑ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ከዚ​ህም በኋላ ደቀ መዛ​ሙ​ርት እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው የሚ​ች​ሉ​ትን ያህል አወ​ጣ​ጥ​ተው በይ​ሁዳ ሀገር ለሚ​ኖ​ሩት ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ርዳ​ታን ይልኩ ዘንድ ወሰኑ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ደቀ መዛሙርትም እያንዳንዳቸው እንደ ችሎታቸው መጠን አዋጥተው በይሁዳ ለሚኖሩት ወንድሞች እርዳታን ይልኩ ዘንድ ወሰኑ፤

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 11:29
27 Referencias Cruzadas  

ብቻ በመካከላቸው ያሉትን ድኾች እንድናስታውስ ዐደራ አሉን፤ ይህም እኔ በትጋት ያደረግኹት ነገር ነው።


ፍቅር ሥርዓተቢስ አያደርግም፤ ፍቅር ያለው ሰው የራሱን ጥቅም ብቻ አይፈልግም፤ ፍቅር ያለው ሰው አይበሳጭም፤ ፍቅር ያለው ሰው ቢበደልም በደልን እንደ በደል አይቈጥርም፤


ባገኘውም ጊዜ ወደ አንጾኪያ አመጣው፤ ሁለቱም አንድ ዓመት ሙሉ ከቤተ ክርስቲያን ጋር በአንድነት ሆነው ብዙ ሰዎችን አስተማሩ፤ ደቀ መዛሙርትም ለመጀመሪያ ጊዜ በአንጾኪያ “ክርስቲያን” ተብለው ተጠሩ።


በይሁዳ ምድር የሚገኙ ሐዋርያትና ወንድሞች አሕዛብ የእግዚአብሔርን ቃል መቀበላቸውን ሰሙ።


መሬት ወይም ቤት ያላቸው ሁሉ እየሸጡ ገንዘቡን ያመጡ ስለ ነበር በመካከላቸው አንድም ችግረኛ አልነበረም።


“ለአሕዛብ ሕዝቦች የተሸጡ አይሁድ ወገኖቻችንን ራሳችን ልንቤዣቸው በማሰብ የሚቻለንን ሁሉ አደረግን፤ እናንተ ደግሞ እነሆ፥ የገዛ ወንድሞቻችሁ የሆኑት አይሁድን ወገኖቻቸው ለሆናችሁት ለእናንተ ባርያዎች አድርገው ራሳቸውን እንዲሸጡላችሁ በማድረግ ላይ ትገኛላችሁ!” ብዬ ገሠጽኳቸው፤ መሪዎቹም የሚመልሱት ቃል አጥተው ዝም አሉ።


እነርሱም ለቤተ መቅደሱ ሥራ ማከናወኛ የሚችሉትን ያኽል አዋጥተው ያቀረቡት ስጦታ ሲደመር አምስት መቶ ኪሎ ወርቅ፥ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ሰማኒያ ስድስት ኪሎ ብር ሆነ፤ ለካህናቱም የሚሆን አንድ መቶ የካህናት ልብስ ሰጡ።


ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሠርጉ ተጠርተው ነበር።


በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ መቶ ኻያ በሚያኽሉ አማኞች መካከል ቆመና እንዲህ አለ፦


ከጥቂት ጊዜ በኋላ የአማኞች ቊጥር እየበዛ ሲሄድ የግሪክ ቋንቋ የሚናገሩ አይሁድ የይሁዳ አገር ተወላጆች በሆኑት አይሁድ ላይ ማጒረምረም ጀመሩ፤ ያጒረመረሙትም በየቀኑ ይታደል በነበረው ርዳታ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች ችላ ይሉባቸው ስለ ነበር ነው።


መብልም በላና በረታ፤ በደማስቆ ከነበሩት ደቀ መዛሙርት ጋር ለጥቂት ቀኖች ቈየ።


ነገር ግን በሌሊት የራሱ ደቀ መዛሙርት ሳውልን በቅርጫት አድርገው በግንቡ አጥር መስኮት ወደታች አወረዱት።


ደቀ መዛሙርቱም በደስታና በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ።


ነገር ግን ደቀ መዛሙርቱ መጥተው በዙሪያው በቆሙ ጊዜ ጳውሎስ ተነሣና ወደ ከተማ ገባ፤ በማግስቱም ከበርናባስ ጋር ወደ ደርቤ ሄደ።


በእነዚያም አገሮች ሁሉ አማኞች በእምነታቸው እንዲጸኑ በማበረታታትና በመምከር “ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት ብዙ መከራ መቀበል አለብን” እያሉ አስተማሩአቸው።


“ከኢየሩሳሌም ከወጣሁ ብዙ ዓመቶች ካለፉ በኋላ ለወገኖቼ የሚሆን የእርዳታ ገንዘብና ለእግዚአብሔር የሚሰጥ መባ ይዤ መጣሁ።


ሁለት መክሊት የተቀበለውም እንዲሁ ሌላ ሁለት መክሊት አተረፈ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios