Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ሳሙኤል 8:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 የጸሩያ ልጅ ኢዮአብ የሠራዊቱ አለቃ ሲሆን የአሒሉድ ልጅ ኢዮሣፍጥ ታሪክ ጸሐፊ ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ የሰራዊቱ አለቃ ሲሆን፣ የአሒሉድ ልጅ ኢዮሣፍጥም ታሪክ ጸሓፊ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ የሠራዊቱ አለቃ ሲሆን፥ የአሒሉድ ልጅ ኢዮሣፍጥም ታሪክ ጸሓፊ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 የሦ​ር​ህያ ልጅ ኢዮ​አ​ብም የሠ​ራ​ዊት አለቃ ነበረ፤ የአ​ሒ​ሎ​ድም ልጅ ኢዮ​ሣ​ፍጥ ታሪክ ጸሓፊ ነበረ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 የጽሩያ ልጅ ኢዮአብም የሠራዊት አለቃ ነበረ፥ የአሒሉድም ልጅ ኢዮሣፍጥ ታሪክ ጸሐፊ ነበረ፥

Ver Capítulo Copiar




2 ሳሙኤል 8:16
10 Referencias Cruzadas  

ከዚህም በኋላ ሦስት ክፍል አድርጎ ላካቸው፤ ኢዮአብን የሢሶው፥ አቢሳይ የሢሶው፥ እንዲሁም የጋት ተወላጅ የሆነው ኢታይ የሢሶው አዛዦች ሆኑ፤ ንጉሡም ተከታዮቹን “እኔም ራሴ አብሬአችሁ እሄዳለሁ” አላቸው።


እንዲሁም ለዐማሳ ሲናገር “አንተም ለእኔ የሥጋ ዘመድ ነህ፤ ከአሁን ጀምሮ በኢዮአብ ምትክ የሠራዊቴ አዛዥ አደርግሃለሁ፤ ይህንንም ባላደርግ እግዚአብሔር በሞት ይቅጣኝ!” ብላችሁ ንገሩት ሲል አዘዛቸው።


እናቱ ጸሩያ ተብላ የምትጠራው ኢዮአብና ሌሎቹም የዳዊት ባለሥልጣኖች ወጥተው በገባዖን ኲሬ ውሃ አጠገብ ተገናኙ፤ ሁሉም በቡድን ተከፋፍለው በኲሬው ውሃ ማዶ ለማዶ ተቀምጠው ነበር።


በዚህ ዐይነት ዳዊት የመላው እስራኤል ንጉሥ ሆኖ ሕዝቡ ዘወትር ትክክለኛ ፍርድ ማግኘት እንዲችል ጥረት ያደርግ ነበር፤


ኤሊሖሬፍና አኪያ የተባሉት የሺሻ ልጆች፥ የቤተ መንግሥት ጸሐፊዎች፤ ኢዮሣፍጥ የተባለው የአሒሉድ ልጅ፥ ታሪክ ጸሐፊና የመዛግብት ኀላፊ፤


ከዚያም በኋላ ወደ ሕዝቅያስ መልእክት ላኩበት፤ ሕዝቅያስም ባለሟሎቹ የሆኑ ሦስት ባለሥልጣኖች ሄደው እንዲገናኙአቸው አዘዘ፤ እነርሱም የቤተ መንግሥቱ ኀላፊ የሆነ የሒልቂያ ልጅ ኤልያቄም፥ እንዲሁም የቤተ መንግሥት ጸሐፊ የሆነው ሼብናና የቤተ መዛግብት ኀላፊ የሆነው የአሳፍ ልጅ ዮአሕ ነበሩ፤


ከዚህ በኋላ ኤልያቄምና ሼብና እንዲሁም ዮአሕ በሐዘን ልብሳቸውን ቀደዱ፤ ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ ቀርበው የአሦራውያን ባለሥልጣን የተናገረውን አስረዱት።


ዳዊትም “በመጀመሪያ በኢያቡሳውያን ላይ አደጋ የሚጥል ሰው የሠራዊቱ አዛዥ ይሆናል!” አለ፤ የጸሩያ ልጅ ኢዮአብ በመጀመሪያ ሄዶ በኢያቡሳውያን ላይ አደጋ በመጣሉ የሠራዊቱ አዛዥ ሆነ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos