Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ሳሙኤል 5:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ዳዊት ከኬብሮን ወደ ኢየሩሳሌም ከመጣ በኋላ ሌሎች ተጨማሪ ሚስቶችና ቁባቶች እንዲኖሩት አደረገ። ብዙ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ተወልደውለት ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ዳዊት ከኬብሮን ከሄደ በኋላ፣ በኢየሩሳሌም ተጨማሪ ሚስቶች አገባ፤ ቁባቶችንም አስቀመጠ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ተወለዱለት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ዳዊት ከኬብሮን ከመጣ በኋላ፥ ከበፊቶቹ በተጨማሪ በኢየሩሳሌም ተጨማሪ ዕቁባቶችን አስቀመጠ፤ ሚስቶችም አገባ፤ ብዙ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ተወለዱለት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ዳዊ​ትም ከኬ​ብ​ሮን ከመጣ በኋላ እንደ ገና ቁባ​ቶ​ቹ​ንና ሚስ​ቶ​ቹን ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወሰደ፤ ለዳ​ዊ​ትም ደግሞ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆች ተወ​ለ​ዱ​ለት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ዳዊትም ከኬብሮን ከመጣ በኋላ ሌሎቹን ቁባቶቹንና ሚስቶቹን ከኢየሩሳሌም ወሰደ፥ ለዳዊትም ደግሞ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ተወለዱለት።

Ver Capítulo Copiar




2 ሳሙኤል 5:13
11 Referencias Cruzadas  

ከእነዚህም ሌላ ዳዊት ከቊባቶቹ የወለዳቸው ሌሎች ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ ትዕማር ተብላ የምትጠራ ሴት ልጅም ነበረችው።


ደግሞም ንጉሡ ብዙ ሚስቶች እንዲኖሩት ማድረግ እግዚአብሔርን ከመከተል ስለሚገታው ንጉሡ ብዙ ሚስቶች እንዲኖሩት አያስፈልገውም፤ ወርቅና ብርም በብዛት አያከማች።


አቢያ ግን ይበልጥ እየበረታ ሄደ፤ ዐሥራ አራት ሚስቶችን አግብቶ ኻያ ሁለት ወንዶች ልጆችንና ዐሥራ ስድስት ሴቶች ልጆችን ወለደ፤


ዳዊትም እግዚአብሔር የእስራኤል ንጉሥ አድርጎ እንዳጸናውና ለሕዝቡም ሲል መንግሥቱን ከፍ እንዳደረገለት ተገነዘበ።


ሰሎሞን የነገሥታት ልጆች የሆኑ ሰባት መቶ ሚስቶችና ሦስት መቶ ቊባቶች ነበሩት፤ እነርሱም ሰሎሞንን ከእግዚአብሔር እንዲርቅ አደረጉት፤


ዳዊት ከዚህ በፊት የኢይዝራኤል ተወላጅ የሆነችውን አሒኖዓምን አግብቶ ነበር፤ አሁን ደግሞ አቢጌልን አገባ፤


ሀብታሙ ሰው ብዙ የቀንድ ከብቶችና የበግ መንጋ ነበሩት፤


ዳዊት በኬብሮን ሳለ የወለዳቸው ወንዶች ልጆች ስም እንደ ዕድሜአቸው ቅደም ተከተል እንደሚከተለው ነው፦ በኲሩ የኢይዝራኤል ተወላጅ ከሆነችው ከአሒኖዓም የተወለደው አምኖን፥ ሁለተኛው የቀርሜሎስ ተወላጅ ከሆነችው ከአቢጌል የተወለደው ዳንኤል፥ ሦስተኛው የገሹር ንጉሥ የታልማይ ልጅ ከሆነችው ከማዕካ የተወለደው አቤሴሎም፥ አራተኛው ከሐጊት የተወለደው አዶንያስ፥ አምስተኛው ከአቢጣል የተወለደው ሸፋጥያ፥ ስድስተኛው ከዔግላ የተወለደው ዩትረዓም፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios