Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ሳሙኤል 19:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 መፊቦሼትም “ንጉሥ ሆይ! ሁሉንም ሀብት ጺባ ይውሰደው፤ ለእኔ አንተ በሰላም ወደ ቤትህ መመለስህ ብቻ ይበቃኛል” አለ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ሜምፊቦስቴም ንጉሡን፣ “ንጉሥ ጌታዬ እንኳን በደኅና ተመለሰ እንጂ፣ እርሱ ሁሉንም ይውሰደው” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ንጉሡም፥ “ነገርህን ለምን ታበዛለህ? አንተና ጺባ እርሻውን ሁሉ እንድትካፈሉ አዝዣለሁ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ሜም​ፌ​ቡ​ስ​ቴም ንጉ​ሡን፥ “ጌታዬ ንጉሡ በደ​ኅና ወደ ቤቱ ከተ​መ​ለሰ እርሱ ሁሉን ይው​ሰ​ደው” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ሜምፊቦስቴም ንጉሡን፦ ጌታዬ ንጉሡ በደኅና ወደ ቤቱ ከተመለሰ እርሱ ሁሉን ይውሰደው አለው።

Ver Capítulo Copiar




2 ሳሙኤል 19:30
7 Referencias Cruzadas  

በፍጹም እንደማላፍር በተስፋ እጠባበቃለሁ፤ ነገር ግን ዘወትር እንደማደርገውና ዛሬ በሕይወት ብኖር ወይም ብሞት ክርስቶስ በሰውነቴ ይከብራል ብዬ በድፍረት እናገራለሁ።


የእግዚአብሔርን የጸጋ ወንጌል ለማስተማር ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልኩትን የማገልገል ግዴታ ከፈጸምኩ ለሕይወቴ ዋጋ አልሰጠውም፤ ለነፍሴም አልሳሳለትም።


“ወንድሜ ዮናታን ሆይ! እኔ ስለ አንተ በጣም አዘንኩ፤ አንተ ለእኔ በጣም ተወዳጅ ነበርክ። ፍቅርህ ለእኔ አስደናቂ ነበር፤ ይኸውም ከሴት ፍቅር የበረታ ነበር።


ንጉሡም “ከዚህ በላይ ብዙ መናገር አያስፈልግህም፤ አንተና ጺባ የሳኦል ንብረት ለሁለት እንድትካፈሉ ወስኛለሁ” ሲል መለሰ።


ገለዓዳዊው ባርዚላይ ንጉሡን አጅቦ የዮርዳኖስን ወንዝ ለመሻገር ከሮገሊም መጣ፤


ከዚህ በኋላ ንጉሡ የሳኦልን አገልጋይ ጺባን ጠርቶ እንዲህ አለው፦ “የሳኦልና የቤተሰቡ ንብረት የነበረውን ማናቸውንም ነገር የጌታህ የልጅ ልጅ ለሆነው ለመፊቦሼት እሰጣለሁ፤


እነርሱም ንጉሡንና ተከታዮቹን በጀልባ አጅበው ወደ ማዶ ለማድረስና ንጉሡ የሚፈልገውን ሁሉ ለማድረግ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻገሩ። ንጉሡ ወንዙን ለመሻገር ሲዘጋጅ ሳለ የጌራ ልጅ ሺምዒ መጥቶ በፊቱ ተዘረጋና እንዲህ አለ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios