Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ሳሙኤል 12:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 መልእክተኞችንም ልኮ ለዳዊት እንዲህ ብለው እንዲነግሩት አደረገ፤ “በራባ ላይ አደጋ ጥዬ የውሃ ማመንጫውን ምሽግ ይዤአለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ከዚያም ኢዮአብ እንዲህ በማለት ወደ ዳዊት መልክተኞችን ላከ፤ “ረባትን ወግቼ የውሃውን ከተማ ይዤአለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ከዚያም ኢዮአብ እንዲህ በማለት ወደ ዳዊት መልክተኞችን ላከ፤ “ራባን ወግቼ የውሃውንም ከተማ ይዤአለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ኢዮ​አ​ብም ወደ ዳዊት እን​ዲህ ብሎ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፥ “ራባ​ትን ወግ​ቻ​ለሁ፤ የው​ኃ​ው​ንም ከተማ ይዤ​አ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ኢዪአብም ወደ ዳዊት፦ ረባትን ወግቻለሁ፥ የውኃውንም ከተማ ይዤአለሁ።

Ver Capítulo Copiar




2 ሳሙኤል 12:27
5 Referencias Cruzadas  

የዓመት መጀመሪያ በሆነው በጸደይ ወራት፥ በተለምዶ ነገሥታት ወደ ጦርነት በሚዘምቱበት ጊዜ፥ ዳዊት ኢዮአብን ከጦር መኰንኖቹና ከመላው የእስራኤል ሠራዊት ጋር አዘመተው፤ እነርሱም ዐሞናውያንን ድል ነሥተው ራባ ተብላ የምትጠራውን ከተማ ከበቡ፤ ዳዊት ግን በኢየሩሳሌም ቈየ።


በዚያን ጊዜ ኢዮአብ ራባ ተብላ የምትጠራውን የዐሞናውያንን ከተማ ለመያዝ የሚያደርገውን ዘመቻ በመቀጠል የከተማ ውሃ የሚገኝበትን ምሽግ ያዘ።


እነሆ አሁን ከሠራዊትህ ቀሪውን ክፍል አሰባስብና በከተማይቱ ላይ አደጋ በመጣል አንተው ራስህ ያዛት፤ አለበለዚያ እኔ ከተማይቱን ይዤ በስሜ እንድትጠራ አደርጋለሁ።”


ለጦሩ ወደ አሞናውያን ከተማ ራባ በሚወስደው መንገድ ላይና እንዲሁም ወደ ተመሸገችው የይሁዳ ከተማ ወደ ኢየሩሳሌም በሚወስደው መንገድ ላይ የአቅጣጫ ምልክት አድርግ።


ከረፋያውያን ወገን ንጉሥ ዖግ የመጨረሻው ነበር፤ አልጋው ከብረት የተሠራ ሆኖ በይፋ በታወቀው መለኪያ ቁመቱ አራት ሜትር፥ የጐኑም ስፋት ሁለት ሜትር ያኽል ነበር። እርሱም ራባ ተብላ በምትጠራው በዐሞናውያን ከተማ እስከ አሁን ይታያል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos