Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ነገሥት 24:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 የባቢሎን ንጉሥ ሰባት ሺህ ለውጊያ ብቃት ያላቸው ወንዶችን፥ እንዲሁም አንድ ሺህ ብረት ቀጥቃጮችንና እደ ጥበበኞችን ወደ ባቢሎን ወሰደ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ደግሞም የባቢሎን ንጉሥ በአጠቃላይ ብርቱ የሆኑትንና ለጦርነት ብቃት ያላቸውን ሰባት ሺሕ ተዋጊዎች፣ አንድ ሺሕ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎችና ቀጥቃጮችን በምርኮ ወደ ባቢሎን ወሰደ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 የባቢሎን ንጉሥ ሰባት ሺህ ለውጊያ ብቃት ያላቸው ወንዶችን፥ እንዲሁም አንድ ሺህ ብረት ቀጥቃጮችንና እደ ጥበበኞችን ወደ ባቢሎን ወሰደ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ሰባት ሺህ ያህል፥ ብር​ቱ​ዎ​ች​ንና ሰልፍ የሚ​ች​ሉ​ትን ሁሉ፥ ኀያ​ላ​ኑን ሁሉ አንድ ሺህ የሚ​ሆኑ ጠራ​ቢ​ዎ​ች​ንና ብረት ሠራ​ተ​ኞ​ች​ንም ወደ ባቢ​ሎን ማረከ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 የባቢሎንም ንጉሥ ብርቱዎቹንና ሰልፍ የሚችሉትን ሁሉ፥ ኀያላኑን ሁሉ ሰባት ሺህ ያህል፥ ጠራቢዎችና ብረት ሠራተኞችም አንድ ሺህ፥ ወደ ባቢሎን ማረከ።

Ver Capítulo Copiar




2 ነገሥት 24:16
8 Referencias Cruzadas  

ናቡከደነፆር የኢየሩሳሌምን ሕዝብ፥ ልዑላን መሳፍንቱን ሁሉና ሌሎችንም ታላላቅ ሰዎችን ጭምር በድምሩ ዐሥር ሺህ ሰዎች ማርኮ ወሰደ፤ ከእነርሱም ጋር የእጅ ጥበብ ዐዋቂዎችንና የብረት አንጣሪዎችን ሁሉ ወሰደ፤ በይሁዳ እንዲቀሩ ያደረገው የመጨረሻዎችን ድኾች ብቻ ነበር።


ነገር ግን ምንም ሀብት የሌላቸውን የመጨረሻ ድኾች፥ አትክልት ኰትኳቾችና መሬት አራሾች ይሆኑ ዘንድ በይሁዳ ምድር ትቶአቸው ሄደ።


የእስራኤል ሕዝብ በየቤተሰቡ ተመዝግቦ ነበር፤ ይህም ታሪክ በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ሰፍሮ ይገኛል። የይሁዳ ሕዝብ በሠራው ኃጢአት ምክንያት በመቀጣት ተማርኮ ወደ ባቢሎን ተወስዶ ነበር፤


ሊገድሉህ ለሚፈልጉና አንተም እጅግ ለምትፈራቸው ሕዝብ፥ ማለትም ለባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርና ለባቢሎናውያን አሳልፌ እሰጥሃለሁ፤


ደብዳቤውንም የጻፍኩት ንጉሡ ኢኮንያን፥ እቴጌይቱ እናቱና የቅርብ አገልጋዮቹ፥ የይሁዳና የኢየሩሳሌም መሪዎች፥ የእጅ ጥበብ ሠራተኞችና ሙያተኞች ሁሉ ተማርከው ከተወሰዱ በኋላ ነው፤


ናቡከደነፆር ማርኮ የወሰዳቸው ሰዎች ብዛት ማስታወሻ ይህ ነው፤ በነገሠ በሰባተኛ ዓመቱ የማረካቸው ሦስት ሺህ ኻያ ሦስት አይሁድ፥


ከንጉሡም ቤተሰብ አንዱን ወስዶ ከእርሱ ጋር የስምምነት ውል አደረገ፤ ለእርሱም ታማኝ እንዲሆንለት በመሐላ ቃል አስገባው፤ ሌሎቹንም የታወቁ ሰዎች ወሰዳቸው።


እኔ ልዑል እግዚአብሔር ለእነርሱ የምለውን ያውቁ ዘንድ ይህን ንገራቸው፤ የተዋቡ ላባዎችና ታላላቅ ክንፎች ያሉት አንድ ግዙፍ ንስር ነበረ፤ ይህም ንስር ወደ ሊባኖስ ተራራዎች በረረ፤ በአንድ የሊባኖስ ዛፍ ላይ አርፎም ጫፉን በመቊረጥ የንግድ ሥራ ወደ ተስፋፋበት ወደ አንድ አገር አምጥቶም ነጋዴዎች በበዙባት ከተማ አኖረው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos