2 ነገሥት 2:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 በዚያም የሚኖሩ የነቢያት ጉባኤ ወደ ኤልሳዕ ሄደው፥ “እግዚአብሔር ዛሬ ጌታህን ከአንተ ለይቶ እንደሚወስደው ታውቃለህን?” ሲሉ ጠየቁት። ኤልሳዕም “አዎ ዐውቃለሁ፤ ነገር ግን ዝም በሉ” ሲል መለሰላቸው። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 በኢያሪኮ የነበሩትም የነቢያት ማኅበር ወደ ኤልሳዕ ወጥተው፣ “ለመሆኑ እግዚአብሔር፣ ጌታህን ኤልያስን ዛሬ ከአንተ ነጥሎ እንደሚወስደው ዐውቀሃልን?” አሉት። እርሱም፣ “አዎን ዐውቄአለሁ፤ እናንተ ግን ዝም በሉ” ሲል መለሰ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 በዚያም የሚኖሩ የነቢያት ጉባኤ ወደ ኤልሳዕ ሄደው፥ “እግዚአብሔር ዛሬ ጌታህን ከአንተ ለይቶ እንደሚወስደው ታውቃለህን?” ሲሉ ጠየቁት። ኤልሳዕም “አዎ ዐውቃለሁ፤ ነገር ግን ዝም በሉ” ሲል መለሰላቸው። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 ወደ ኢያሪኮም ደረሱ፤ በኢያሪኮም የነበሩ የነቢያት ልጆች ወደ ኤልሳዕ ቀርበው፥ “እግዚአብሔር ጌታህን ከራስህ ላይ ዛሬ እንዲወስደው ዐውቀሃልን?” አሉት። እርሱም፥ “አዎን፥ ዐውቄአለሁ፤ ዝም በሉ” አላቸው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 በኢያሪኮም የነበሩ የነቢያት ልጆች ወደ ኤልሳዕ ቀርበው “እግዚአብሔር ጌታህን ከራስህ ላይ ዛሬ እንዲወስደው አውቀሃልን?” አሉት። እርሱም “አዎን፥ አውቄአለሁ፤ ዝም በሉ፤” ብሎ መለሰ። Ver Capítulo |