2 ነገሥት 19:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 በመልክተኞችህ አማካይነት፥ በእግዚአብሔር ላይ ስድብህን ከምረሃል፤’ ‘በሠረገሎቼ ከፍተኛ ወደ ሆኑት ተራራዎች፤ ወደ ሊባኖስ ጫፍ ወጥቼአለሁ፤ ረጃጅሞቹን የሊባኖስ ዛፎችዋንና ምርጦች ዝግባ ቈርጬአለሁ፤ ወደ ዳርቻዋና ውብ ወደ ሆነው ጫካዋ ደርሼአለሁ፤’ ብለሃል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም23 በመልእክተኞችህ በኩል፣ በጌታ ላይ የስድብ ቃል ተናገርህ፤ እንዲህም አልህ፤ “በሠረገሎቼ ብዛት፣ የተራሮችንም ከፍታ፣ የሊባኖስንም ጫፍ ወጥቻለሁ፤ ረዣዥም ዝግባዎችን፣ የተመረጡ ጥዶችን ቈርጫለሁ፤ እጅግ ወደራቁት፣ እጅግ ውብ ወደሆኑትም ደኖች ደርሻለሁ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 በመልክተኞችህ አማካይነት፥ በእግዚአብሔር ላይ ስድብህን ከምረሃል፤’ ‘በሠረገሎቼ ከፍተኛ ወደ ሆኑት ተራራዎች፤ ወደ ሊባኖስ ጫፍ ወጥቼአለሁ፤ ረጃጅሞቹን የሊባኖስ ዛፎችዋንና ምርጦች ዝግባ ቆርጬአለሁ፤ ወደ ዳርቻዋና ውብ ወደ ሆነው ጫካዋ ደርሼአለሁ፤’ ብለሃል። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 አንተስ በመልእክተኞችህ እጅ በእግዚአብሔር ላይ ተገዳደርህ፤ እንዲህም አልህ፦ በሰረገላዬ ብዛት ወደ ተራሮች ከፍታ፥ ወደ ሊባኖስ ጥግ እወጣለሁ፤ ረጃጅሞችንም ዝግባዎች የተመረጡትንም ጥዶች እቈርጣለሁ፤ ወደ ሀገሩም ዳርቻና ወደ ቀርሜሎስ ዱር እገባለሁ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 አንተስ “በሠረገላዬ ብዛት ወደ ተራሮች ከፍታ፥ ወደ ሊባኖስ ጥግ ላይ ወጥቻለሁ፤ ረጃጅሞቹንም ዝግባዎች የተመረጡትንም ጥዶች እቈርጣለሁ፤ ወደ አገሩም ዳርቻና ወደ ቀርሜሎስ ዱር እገባለሁ። Ver Capítulo |