Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ነገሥት 12:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20-21 ከዚህ በኋላ የንጉሥ ኢዮአስ ባለሟሎች የሆኑ ባለሥልጣኖች አደሙበት፤ ከእነርሱም ሁለቱ የሺምዓት ልጅ ዮዛካርና የሾሜር ልጅ ይሆዛባድ ወደ ሲላ በሚወስደው ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ በሚገኘው በተደለደለ መሬት ላይ በተሠራው ቤት ገደሉት፤ ኢዮአስም በዳዊት ከተማ በሚገኘው በነገሥታት መካነ መቃብር ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ አሜስያስ ነገሠ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ሹማምቱም በርሱ ላይ ዐመፁበት፤ ቍልቍል ወደ ሲላ በሚወስደው መንገድ ላይ በቤት ሚሎ ገደሉት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 የቀረውም የኢዮአስ ነገር፥ የሠራውም ሥራ ሁሉ፥ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም ተነ​ሥ​ተው ዐመ​ፁ​በት፥ ወደ ሲላ በሚ​ወ​ር​ደ​ውም መን​ገድ በመ​ሀሎ ቤት ኢዮ​አ​ስን ገደ​ሉት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 የቀረውም የኢዮአስ ነገር፥ የሠራውም ሥራ ሁሉ፥ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?

Ver Capítulo Copiar




2 ነገሥት 12:20
11 Referencias Cruzadas  

ዳዊት ምሽጉን ከያዘ በኋላ መኖሪያውን በዚያው ስፍራ አደረገ፤ እርስዋንም “የዳዊት ከተማ” ብሎ ጠራት፤ ከኮረብታው በስተ ምሥራቅ በኩል በዐፈር ከተደለደለው ስፍራ አንሥቶ በኮረብታው ዙሪያ ከተማይቱንም ሠራ።


ኢዮርብዓም ለዐመፅ የተነሣሣበትም ታሪክ እንደሚከተለው ነው፥ በዚያን ጊዜ ሰሎሞን ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ ሚሎ ተብሎ የሚጠራውን ጐድጓዳ ስፍራ በመሙላት እየደለደለና የአባቱን የዳዊትን ከተማ ቅጽሮች እየጠገነ በማደስ ላይ ነበር።


ንጉሥ ሮብዓም ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፤


ንጉሥ ኢዮአስ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተመዝግቦ ይገኛል።


አሜስያስ መንግሥቱን አደላድሎ እንደ ያዘ ወዲያውኑ፥ ቀደም ሲል ነግሦ የነበረውን አባቱን የገደሉትን ባለሥልጣኖች በሞት ቀጣ፤


ባለሟሎቹ የሆኑ ባለሥልጣኖችም በአሞን ላይ አድመው በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ገደሉት፤


ኢዮራም ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፤


አሜስያስ እግዚአብሔርን ከተወበት ጊዜ ጀምሮ በኢየሩሳሌም ውስጥ እርሱን ለመግደል ሤራ ተጠንስሶ ነበር፤ በመጨረሻም አሜስያስ ሸሽቶ ወደ ላኪሽ ሄደ፤ ነገር ግን ጠላቶቹ እዚያው ድረስ ልከው አስገደሉት፤


የአሞን ባለሟሎች የሆኑት ባለሥልጣኖች በእርሱ ላይ በማሤር በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ገደሉት፤


ከዚያን በኋላ የሴኬምና የቤትሚሎ ሕዝብ በአንድነት ተሰብስበው፥ በሴኬም ወደሚገኘው ወደተቀደሰው ወርካ ዛፍ ሄዱ፤ በዚያም አቤሜሌክን አነገሡ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos