Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ነገሥት 1:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ኤልያስም “እኔስ የእግዚአብሔር ሰው ከሆንኩ እሳት ከሰማይ ወርዶ አንተንና ኀምሳውን ሰዎችህን ይብላ!” አለው፤ በዚያም ጊዜ ወዲያውኑ እሳት ከሰማይ ወርዶ መኰንኑንና ኀምሳዎቹን ሰዎች በላ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ኤልያስም መልሶ የዐምሳ አለቃውን፣ “እኔ የእግዚአብሔር ሰው ከሆንሁ፣ እሳት ከሰማይ ወርዳ፣ አንተንና ዐምሳውን ሰዎችህን ትብላ!” አለው። ከዚያም እሳት ከሰማይ ወርዳ የዐምሳ አለቃውንና ሰዎቹን ፈጽማ በላች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ኤልያስም “እኔስ የእግዚአብሔር ሰው ከሆንኩ እሳት ከሰማይ ወርዶ አንተንና ኀምሳውን ሰዎችህን ይብላ!” አለው፤ በዚያም ጊዜ ወዲያውኑ እሳት ከሰማይ ወርዶ መኰንኑንና ኀምሳዎቹን ሰዎች በላ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ኤል​ያ​ስም መልሶ የአ​ምሳ አለ​ቃ​ውን፥ “እኔስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው እንደ ሆንሁ እሳት ከሰ​ማይ ትው​ረድ፤ አን​ተ​ንም፥ አም​ሳ​ው​ንም ሰዎ​ች​ህን ትብላ” አለው። እሳ​ትም ከሰ​ማይ ወርዳ እር​ሱ​ንና አም​ሳ​ውን ሰዎች በላች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ኤልያስም መልሶ የአምሳ አለቃውን “እኔስ የእግዚአብሔር ሰው እንደ ሆንሁ እሳት ከሰማይ ትውረድ፤ አንተንም፥ አምሳውንም ሰዎችህን ትብላ፤” አለው። እሳትም ከሰማይ ወርዳ እርሱንና አምሳ ሰዎቹን በላች።

Ver Capítulo Copiar




2 ነገሥት 1:10
22 Referencias Cruzadas  

ሚክያስም “አንተ በደኅና ከተመለስክማ እግዚአብሔር በእኔ አማካይነት አልተናገረም ማለት ነዋ!” አለው፤ ቀጥሎም ድምፁን ከፍ በማድረግ “በዚህ የምትገኙ ሕዝቦች ሁሉ እኔ የተናገርኩትን ሁሉ ልብ ብላችሁ አድምጡ!” አለ።


ንጉሡም እንደገና ሌላውን መኰንን ከኀምሳ ሰዎች ጋር ላከ፤ እርሱም ወደ ኤልያስ ወጥቶ “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! አሁኑኑ ወርደህ ወደ እርሱ እንድትመጣ ንጉሡ አዞሃል!” አለው።


እስራኤላውያን ግን በእግዚአብሔር መልእክተኞች ላይ ተሳለቁ፤ በነቢያቱም በማፌዝ፥ የእግዚአብሔርን ቃል አቃለሉ፤ ከዚህም የተነሣ፥ የእግዚአብሔር ቊጣ በሕዝቡ ላይ ወረደ፤ ከታላቅ ቊጣውም ለማምለጥ አልቻሉም።


የመጀመሪያው መልእክተኛ ንግግሩን ገና ሳይጨርስ ሌላ መልእክተኛ መጣና “በጎቹንና እረኞቹን በሙሉ መብረቅ ከሰማይ ወርዶ ገደላቸው፤ እኔ ብቻ አምልጬ የሆነውን ነገር ልነግርህ መጣሁ” አለው።


“የተመረጡ አገልጋዮቼን አትንኩ፤ ነቢያቴንም አትጒዱ” በማለት አስጠነቀቃቸው።


በተከታዮቻቸውም ላይ እሳት ወረደ፤ እነዚያንም ክፉ ሰዎች አቃጠለ።


ንጉሡ በሰጠው ጥብቅ ትእዛዝ መሠረት እሳቱ በኀይል ተቀጣጥሎ ይነድ ስለ ነበር ሲድራቅን፥ ሚሳቅንና አብደናጎን ወደ እሳቱ የጣሉአቸውን ሰዎች የእሳቱ ወላፈን አቃጥሎ ገደላቸው።


ንጉሡም “እነሆ፥ እኔ እሳቱ ምንም ሳይጐዳቸው ከእስራት ተፈተው በነበልባሉ ውስጥ የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ፤ አራተኛውም የአማልክትን ልጅ ይመስላል” አለ።


ከዚህም በኋላ ዳንኤልን የከሰሱት ሰዎች ተይዘው እንዲመጡ ንጉሡ አዘዘ፤ እነርሱም ተይዘው ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር በአንበሶች ጒድጓድ ውስጥ እንዲጣሉ አደረገ፤ ገና ወደ ጒድጓዱ አዘቅት ሳይደርሱም አንበሶቹ ቦጫጨቋቸው፤ አጥንቶቻቸውንም ሁሉ ሰባበሩ።


ከዚህም የተነሣ በድንገት ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከ እሳት ስለ በላቸው በእግዚአብሔር ፊት ሞቱ፤


እስራኤላውያን ስለ ደረሰባቸው ችግር ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ ማጒረምረም ጀመሩ፤ እግዚአብሔርም የማጒረምረም ጩኸታቸውን ሰምቶ እጅግ በመቈጣት የሚባላ እሳት ላከባቸው፤ ያም እሳት ከሰፈሩ አንዱን ክፍል አወደመ።


ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር እሳት ልኮ ዕጣን ያጥኑ የነበሩትን ሁለት መቶ ኀምሳ ሰዎች አቃጠለ።


እነርሱም “የእነዚህን ክፉ ሰዎች ፍጻሜ የከፋ ያደርገዋል። የወይኑንም ተክል ቦታ ፍሬውን በየጊዜው ለሚሰጡት ለሌሎች ገበሬዎች ያከራያል” አሉት።


ደቀ መዛሙርቱ ያዕቆብና ዮሐንስ ይህን ባዩ ጊዜ፥ “ጌታ ሆይ! ከሰማይ እሳት ወርዶ እነዚህን ሰዎች ያቃጥላቸው ዘንድ እንድናዝዝ ትፈቅዳለህን?” አሉት።


ሄሮድስም በበኩሉ ጴጥሮስን አስፈልጎ ባጣው ጊዜ ዘብ ጠባቂዎችን ከመረመረ በኋላ እንዲገደሉ አዘዘ፤ ከዚህም በኋላ ሄሮድስ ከይሁዳ ወደ ቂሳርያ ሄዶ እዚያ ተቀመጠ።


አምላካችን እንደሚያቃጥል እሳት ነው።


ማንም እነርሱን ሊጐዳ ቢፈልግ እሳት ከአፋቸው ወጥቶ ጠላቶቻቸውን ያቃጥላል፤ እነርሱን ሊጐዳ የሚፈልግ ሁሉ የሚሞተው በዚህ ዐይነት ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos