Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ቆሮንቶስ 11:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ሦስት ጊዜ በዱላ ተደብድቤአለሁ፤ አንድ ጊዜ በድንጋይ ተወግሬአለሁ፤ ሦስት ጊዜ የመርከብ አደጋ ደርሶብኛል፤ አንድ ሌሊትና አንድ ቀን በባሕር ላይ ነበርኩ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ሦስት ጊዜ በዱላ ተደብድቤአለሁ፤ አንድ ጊዜ በድንጋይ ተወግሬአለሁ፤ ሦስት ጊዜ የመርከብ አደጋ ደርሶብኛል፤ አንድ ሌሊትና ቀን በባሕር ላይ ዐድሬአለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ሦስት ጊዜ በበትር ተመትቻለሁ፤ አንድ ጊዜ በድንጋይ ተወግሬለሁ፤ መርከቤ ሦስት ጊዜ ተሰባብሯል፤ ሌሊትና ቀን በባሕር ውስጥ ኖሬለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ሦስት ጊዜ በበ​ትር ደበ​ደ​ቡኝ፤ አንድ ጊዜ በድ​ን​ጋይ መቱኝ፤ መር​ከቤ ሦስት ጊዜ ተሰ​በ​ረች፤ በጥ​ልቁ ባሕር ውስጥ ስዋኝ አድሬ፥ ስዋኝ ዋልሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ሦስት ጊዜ በበትር ተመታሁ፤ አንድ ጊዜ በድንጋይ ተወገርሁ፤ መርከቤ ሦስት ጊዜ ተሰበረ፤ ሌሊትና ቀን በባሕር ውስጥ ኖርሁ።

Ver Capítulo Copiar




2 ቆሮንቶስ 11:25
12 Referencias Cruzadas  

አይሁድ ግን ከአንጾኪያና ከኢቆንዮን ወደዚያ መጥተው ሕዝቡን አሳደሙና ጳውሎስን በድንጋይ እንዲወግሩት አደረጉ፤ የሞተ መስሎአቸውም ጐትተው ከከተማ አወጡት።


በድንጋይ ተወገሩ፤ በመጋዝ ተሰነጠቁ፤ በሰይፍ ተገደሉ፤ የበግና የፍየል ቆዳ ለብሰው ተንከራተቱ፤ ድኾችና ስደተኞች ሆነው ተንገላቱ፤


ጳውሎስ ግን “እኛ የሮም ዜጋዎች ስንሆን ያለ ፍርድ በአደባባይ ገርፈው ወደ ወህኒ አስገብተውናል። አሁን ደግሞ ከወህኒ ቤት በስውር እንድንወጣ ያደርጋሉን? አይሆንም! እነርሱ ራሳቸው መጥተው ያስወጡን!” ሲል መለሰ።


በዚያኑ ሰዓት በሌሊት የወህኒ ቤቱ ጠባቂ ወሰዳቸውና ቊስላቸውን አጠበላቸው፤ ወዲያውኑ እርሱና ቤተሰቡ በሙሉ ተጠመቁ።


አሕዛብና አይሁድ ከአለቆቻቸው ጋር ሆነው ጳውሎስንና በርናባስን ሊያንገላቱአቸውና በድንጋይ ሊወግሩአቸው ፈለጉ፤


ገበሬዎቹ ግን አገልጋዮቹን ይዘው አንዱን ደበደቡት፤ አንዱን ገደሉት፤ ሌላውን ደግሞ በድንጋይ ወገሩት።


አዛዡ ይህን ባየ ጊዜ ጳውሎስን ወደ ወታደሮች ሰፈር እንዲያስገቡት አዘዘ፤ ሕዝቡ በእርሱ ላይ ስለምን ይህን ያኽል እንደሚጮኹ ለማወቅም እየተገረፈ እንዲመረመር አዘዘ።


ለአሕዛብም አሳልፈው ይሰጡታል፤ እነርሱም ያላግጡበታል፤ ይገርፉታል፤ ይሰቅሉታልም፤ ግን በሦስተኛው ቀን ከሞት ይነሣል።”


እምነትና መልካም ኅሊና ይኑርህ። አንዳንድ ሰዎች ኅሊናቸውን በመጣላቸው መርከብ በማዕበል እንደሚጠፋ እምነታቸውን አጥፍተዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios