Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ቆሮንቶስ 10:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 የእናንተ ታዛዥነት ፍጹም ሲሆን ማንኛውንም አለመታዘዝ ለመቅጣት ዝግጁዎች እንሆናለን።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 መታዘዛችሁ በተፈጸመ ጊዜ አለ መታዘዝን ሁሉ ለመቅጣት ተዘጋጅተናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 መታዘዛችሁም በተፈጸመች ጊዜ አለመታዘዝን ሁሉ ልንበቀል ተዘጋጅተናል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እና​ንተ ትእ​ዛ​ዝን በፈ​ጸ​ማ​ችሁ ጊዜ የማ​ይ​ገ​ዛ​ውን ሁሉ እኛ ልን​በ​ቀ​ለው ዝግ​ጁ​ዎች ነን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 መታዘዛችሁም በተፈጸመች ጊዜ አለመታዘዝን ሁሉ ልንበቀል ተዘጋጅተናል።

Ver Capítulo Copiar




2 ቆሮንቶስ 10:6
12 Referencias Cruzadas  

አንተ በእግዚአብሔር ሕግ ትመካለህ፤ ነገር ግን ሕጉን በማፍረስ እግዚአብሔርን ትንቃለህ።


የምትፈልጉት ምንድን ነው? የመቅጫ በትር ይዤ ወደ እናንተ እንድመጣ ትፈልጋላችሁን? ወይስ በፍቅርና በትሕትና መንፈስ እንድመጣ ትፈልጋላችሁ?


ይህን መልእክት ከእናንተ ርቄ ሳለሁ የጻፍኩላችሁ በዚሁ ምክንያት ነው፤ በዚህ ዐይነት ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ ጌታም በሰጠኝ ሥልጣን አላስጨንቃችሁም፤ ጌታ ሥልጣን የሰጠኝ እናንተን ለማነጽ እንጂ እናንተን ለማፍረስ አይደለም።


በሁለተኛው ጒብኝቴ ከእናንተ ጋር በነበርኩ ጊዜ በማስጠንቀቅ ተናግሬ ነበር፤ አሁንም ደግሞ በሩቅ ሆኜ ከዚህ ቀደም ኃጢአት ለሠሩትና ለሌሎችም በማስጠንቀቅ እናገራለሁ፤ አሁን ወደ እናንተ ተመልሼ በምመጣበት ጊዜ ለማንም አልራራም፤


ያንንም መልእክት የጻፍኩላችሁ ተፈትናችሁ በሁሉ ነገር ታዛዦች መሆናችሁን ለመረዳት ብዬ ነው።


ሁላችሁም ታዛዦች እንደ ሆናችሁና በፍርሃትና በመንቀጥቀጥም እንደ ተቀበላችሁት ቲቶ ሲያስታውስ፥ ለእናንተ ያለው ፍቅር በጣም ታላቅ ሆኖአል።


ከእነርሱ መካከል ሄሜኔዎስና እስክንድር ይገኛሉ፤ እነርሱ በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል ከመናገር መቈጠብን እንዲማሩ ለሰይጣን አሳልፌ ሰጥቼአቸዋለሁ።


ስለዚህ ወደ እናንተ ስመጣ እርሱ እየሰደበንና እያዋረደን ያደረገውን ክፉ ሥራ ሁሉ ለሁሉም እናገራለሁ፤ ይህም ሳይበቃው ቀርቶ፤ እርሱ ራሱ ወንድሞችን አይቀበልም። ሌሎችም እንዳይቀበሉአቸው ይከለክላል። ከቤተ ክርስቲያንም ያስወጣቸዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos