Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 9:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እርሱም ላቀረበችለት ጥያቄ ሁሉ መልስ ሰጠ፤ ሊተረጒምላት የተሳነውና ከእርሱ የተሰወረ ምንም ዐይነት እንቆቅልሽ አልነበረም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ሰሎሞንም የጠየቀችውን ሁሉ መለሰላት፤ ከሰሎሞን የተሰወረና ሊመልስላት ያልቻለው አንድም ጥያቄ አልነበረም

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ሰሎሞንም የጠየቀችውን ሁሉ ፈታላት፤ ሰሎሞንም ያልፈታው ስውር ነገር አልነበረም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ሰሎ​ሞ​ንም የጠ​የ​ቀ​ች​ውን ሁሉ ፈታ​ላት፤ ሰሎ​ሞ​ንም ያል​ፈ​ታው ነገር አል​ነ​በ​ረም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ሰሎሞንም የጠየቀችውን ሁሉ ፈታላት፤ ሰሎሞንም ያልፈታው ስውር ነገር አልነበረም።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 9:2
12 Referencias Cruzadas  

እነሆ የጠየቅኸውን አደርጋለሁ፤ እንዲያውም ማንም ሰው ከዚህ በፊት ካገኘውና ወደ ፊትም ሊያገኘው ከሚችለው የሚበልጥ ጥበብንና አስተዋይነትን እሰጥሃለሁ፤


እግዚአብሔር ለሰሎሞን እጅግ አስደናቂ የሆነ ጥበብንና አስተዋይነትን እንዲሁም ወሰን የማይገኝለትን ዕውቀት ሰጠው፤


ንግሥተ ሳባ ስለ ሰሎሞን የሚነገረውን አስደናቂ ጥበብ ሁሉ ሰማች፤ ስለዚህ አስቸጋሪ በሆኑ የእንቆቅልሽ ጥያቄዎች ልትፈትነው ወደ ኢየሩሳሌም መጣች፤ ወደ ኢየሩሳሌም ስትመጣም ብዙ የክብር አጃቢዎችን አስከትላ ሽቶ፥ የከበሩ ዕንቆችና እጅግ የበዛ ወርቅ በግመሎች አስጭና ነበር፤ ከሰሎሞንም ጋር በተገናኘች ጊዜ በሐሳብዋ የነበረውን ጥያቄ ሁሉ አቀረበችለት፤


ንግሥተ ሳባም ጥበብ የተሞላበትን የሰሎሞንን አነጋገር አዳመጠች፤ እርሱ ያሠራውንም ቤተ መንግሥት አየች፤


ከጥበበኞች የሚወዳጅ ጥበበኛ ይሆናል። ማስተዋል ከጐደላቸው ሰዎች ጋር ጓደኛ የሚሆን ግን ይጐዳል።


ከሰው አንደበት የሚወጣው የጥበብ ንግግር እንደ ጥልቅ ውሃ ነው፤ እንደ ምንጭ ውሃም ጣፋጭ ነው።


እርሱም እንዲህ አላቸው፦ “ለእናንተ የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፤ በውጪ ላሉት ግን ሁሉ ነገር በምሳሌ ይነገራቸዋል።


ያለ ምሳሌም አያስተምራቸውም ነበር፤ ብቻቸውን ሲሆኑ ግን ሁሉን ነገር ለደቀ መዛሙርቱ ያስረዳቸው ነበር።


አገልጋይ ጌታው የሚያደርገውን ስለማያውቅ ከእንግዲህ ወዲህ አገልጋዮች አልላችሁም፤ ነገር ግን ከአባቴ የሰማሁትን ሁሉ ስለ ገለጥኩላችሁ ወዳጆቼ ብያችኋለሁ፤


የጥበብና የዕውቀት ሀብት ተሰውሮ የሚገኘው በክርስቶስ ዘንድ ነው።


የእግዚአብሔር ቃል ሕያውና የሚሠራ ነው፤ ሁለት አፍ ካለው ሰይፍ ይልቅ ስለታም ነው፤ ነፍስንና መንፈስን፥ ጅማትንና ቅልጥምን እስኪለያይ ድረስ የሚቈራርጥ ነው፤ በልብ ውስጥ የተሰወረውንም ሐሳብና ምኞት መርምሮ የሚፈርድ ነው።


ከእናንተ መካከል ጥበብ የጐደለው ሰው ቢኖር እግዚአብሔርን ይለምን፤ እግዚአብሔርም ይሰጠዋል፤ እርሱ ምንም ቅር ሳይለው ለሁሉም በልግሥና የሚሰጥ ቸር አምላክ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos