Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 24:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 የኢዮአስ ልጆች ታሪክ፥ በኢዮአስ ላይ ተነግረው የነበሩት የትንቢት ቃላትና ኢዮአስ ቤተ መቅደሱን እንዴት እንዳደሰ በነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ መግለጫ ውስጥ ተመዝግቦ ይገኛል፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ አሜስያስ ነገሠ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 የወንዶች ልጆቹ ታሪክ፣ ስለ እርሱ የተነገሩት ብዙ ትንቢቶችና የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መታደስ በነገሥታቱ የታሪክ መዛግብት ተጽፈዋል። ልጁ አሜስያስም በርሱ ፈንታ ነገሠ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 የልጆቹና በእርሱ ላይ የተደረገው ነገር የጌታንም ቤት ማደሱ፥ እነሆ፥ በነገሥታቱ መጽሐፍ ተጽፎአል። ልጁም አሜስያስ በእርሱ ፋንታ ነገሠ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 የል​ጆ​ቹና በእ​ርሱ ላይ የተ​ደ​ረ​ገው ነገር፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት ማደሱ፥ እነሆ በነ​ገ​ሥ​ታቱ የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል። ልጁም አሜ​ስ​ያስ በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 የልጆቹና በእርሱ ላይ የተደረገው ነገር የእግዚአብሔርንም ቤት ማደሱ፥ እነሆ፥ በነገሥታቱ መጽሐፍ ተጽፎአል። ልጁም አሜስያስ በእርሱ ፋንታ ነገሠ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 24:27
10 Referencias Cruzadas  

የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአስም ከእርሱ በፊት የነበሩትን ነገሥታት፥ ማለትም ኢዮሣፍጥ፥ ኢዮራምና አካዝያስ ለእግዚአብሔር ለይተው ያኖሩትን መባና የራሱን መባ ጨምሮ በቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥት ግምጃ ቤቶች የነበረውን ወርቅ ሁሉ በመሰብሰብ ገጸ በረከት አድርጎ ለንጉሥ አዛሄል ላከለት፤ ሐዛኤልም ይህን ተቀብሎ ሠራዊቱን ከኢየሩሳሌም መለሰ።


አሜስያስ፥ ዐዛርያስ፥ ኢዮአታም፥


የቀረው የንጉሥ አቢያ ታሪክ፥ እርሱ የተናገራቸው ቃላትና ያከናወነው ሥራ ሁሉ፥ በነቢዩ ዒዶ የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተመዝግቦ ይገኛል።


በአሳ ዘመነ መንግሥት ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ የተፈጸሙ ድርጊቶች ሁሉ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጻሕፍት ተመዝግበው ይገኛሉ፤


ኢዮሣፍጥ ከነገሠበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ዘመነ መንግሥቱ ፍጻሜ ድረስ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ ከእስራኤል ነገሥታት ታሪክ ክፍል አንዱ በሆነው በሐናኒ ልጅ በኢዩ ታሪክ ውስጥ ተመዝግቦ ይገኛል።


ንጉሡና ካህኑ ዮዳሄ ገንዘቡን የቤተ መቅደሱ እድሳት ኀላፊዎች ለሆኑት ሰዎች ይሰጡአቸው ነበር፤ እነዚህም ኀላፊዎች ገንዘቡን ቤተ መቅደሱን የሚጠግኑ ግንበኞችን፥ አናጢዎችንና ብረታ ብረት ሠራተኞችን ይቀጥሩበት ነበር፤


በንጉሡ ላይ ያሤሩትም ሺምዓት ተብላ የምትጠራ የዐሞን ተወላጅ ልጅ የሆነው ዛባድና ሺምሪት ተብላ የምትጠራ የሞአብ ተወላጅ ልጅ የሆነው ይሆዛባድ ናቸው።


አሜስያስ ዕድሜው ኻያ አምስት ዓመት ሲሆን ነገሠ፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ኻያ ዘጠኝ ዓመት ገዛ፤ እናቱ ይሆዓዲን ተብላ የምትጠራ የኢየሩሳሌም ተወላጅ ነበረች፤


ሌላው የሰሎሞን ታሪክ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በነቢዩ ናታን ታሪክ፥ የሴሎ ተወላጅ በሆነው በነቢዩ አኪያ ትንቢትና ስለ እስራኤል ንጉሥ ኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት ጭምር በሚናገረው በነቢዩ ዒዶ ራእይ ተመዝግቦ ይገኛል፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios