2 ዜና መዋዕል 20:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም24 የይሁዳ ሠራዊት በረሓውን የሚያሳይ ከፍተኛ ቦታ በደረሱ ጊዜ ጠላቶቹ ወዳሉበት አቅጣጫ ሲመለከቱ ጠላቶቹ በሙሉ አልቀው ሬሳዎቻቸው በምድር ላይ ተጋድመው አዩ፤ አንድም እንኳ በሕይወት ተርፎ ያመለጠ አልነበረም። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም24 የይሁዳ ሰዎች ምድረ በዳውን ቍልቍል ወደሚያሳየው ቦታ መጥተው ግዙፉን ሰራዊት ሲመለከቱ፣ መሬቱ ሬሳ በሬሳ ሆኖ አዩ፤ አንድም ሰው አላመለጠም። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)24 የይሁዳም ሰዎች በምድረ በዳ ወዳለው የመጠበቅያ ግንብ በመጡ ጊዜ ሕዝቡን አዩ፤ እነሆም፥ በምድሩ ሁሉ ሬሳ ሞልቶ ነበር፥ ያመለጠም ሰው አልነበረም። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)24 የይሁዳም ሰዎች ወደ ምድረ በዳው መጠበቂያ ግንብ በመጡ ጊዜ ሕዝቡን አዩ፤ እነሆም፥ በምድሩ ሁሉ ሬሳ ሞልቶ ነበር፤ ያመለጠም ሰው አልነበረም። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)24 የይሁዳም ሰዎች ወደ ምድረ በዳ ግንብ በመጡ ጊዜ ሕዝቡን አዩ፤ እነሆም፥ በምድሩ ሁሉ ሬሳ ሞልቶ ነበር፤ ያመለጠም ሰው አልነበረም። Ver Capítulo |