Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ጢሞቴዎስ 1:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ይህንንም የሚያደርጉት የሕግ መምህራን ለመሆን ፈልገው ነው፤ ይሁን እንጂ የሚናገሩትን አያውቁም ወይም እርግጠኞች ነን የሚሉበትንም ነገር አያስተውሉም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 የሕግ መምህራን ለመሆን ይፈልጋሉ፤ ሆኖም ስለሚናገሩት ወይም አስረግጠው ስለሚሟገቱለት ነገር አያውቁም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ምን እንደሚናገሩ ወይም በምን ዓይነት ነገሮች ላይ በድፍረት ማረገጋገጫ እንደሚሰጡ ሳያስተውሉ የሕግ አስተማሪዎች መሆንን ይፈልጋሉ።

Ver Capítulo Copiar




1 ጢሞቴዎስ 1:7
20 Referencias Cruzadas  

እነርሱ ዕውሮችና ዕውሮችን የሚመሩ ስለ ሆኑ ተዉአቸው፤ ዕውር ዕውርን ቢመራ ሁለቱም በጒድጓድ ውስጥ ይወድቃሉ።”


ስለዚህ “አናውቅም” ሲሉ ለኢየሱስ መለሱለት። እርሱም “እንግዲያውስ እኔም በምን ሥልጣን ይህን ሁሉ እንደማደርግ አልነግራችሁም” አላቸው።


ከሦስት ቀንም በኋላ በቤተ መቅደስ አገኙት፤ በዚያም በሊቃውንት መካከል ተቀምጦ ሲያዳምጣቸውና ጥያቄም ሲያቀርብላቸው ነበር።


አንዳንድ ሰዎች ከይሁዳ ወደ አንጾኪያ ሄደው፥ “ለሙሴ በተሰጠው ሕግ መሠረት ካልተገረዛችሁ ልትድኑ አትችሉም” እያሉ አማኞችን ያስተምሩ ጀመር።


“ጥበበኞች ነን” ሲሉ ሞኞች ሆኑ።


ማወቅ የምፈልገው ይህን ብቻ ነው፤ ለመሆኑ እናንተ መንፈስ ቅዱስን የተቀበላችሁት ሕግን በመፈጸም ነውን? ወይስ የምሥራቹን ቃል ሰምታችሁ በማመን ነው?


እግዚአብሔር መንፈሱን የሚሰጣችሁና በእናንተ ዘንድ ተአምራትን የሚያደርገው ሕግን በመፈጸማችሁ ነውን? ወይስ የምሥራቹን ቃል ሰምታችሁ በማመናችሁ ነው?


እናንተ ለሕግ ተገዢዎች ሆናችሁ መኖር የምትፈልጉ እስቲ ንገሩኝ፤ ሕግ የሚለውን አትሰሙምን?


በትዕቢት የተወጠረና ምንም የማያውቅ ነው፤ ነገር ግን ስለ ቃላት የመከራከርና የመጨቃጨቅ ክፉ ምኞት አድሮበታል፤ ይህም የሚያስከትለው ቅንአትን፥ ጠብን፥ ስድብን፥ መጥፎ ጥርጣሬን፥


እንዲህ ዐይነቶቹ ሴቶች ሁልጊዜ ይማራሉ፤ ነገር ግን እውነትን ወደ ማወቅ መድረስ አይችሉም።


ወንድሞቼ ሆይ! እኛ አስተማሪዎች የሆንን የባሰ ፍርድ እንደምንቀበል ታውቃላችሁና ከእናንተ ብዙዎች አስተማሪዎች አይሁኑ።


እነዚህ ሐሰተኞች መምህራን ግን ለማስተዋል ያቃታቸውን ነገር ይሳደባሉ፤ እነርሱ ለመጠመድና ለመገደል እንደ ተወለዱ፥ በተፈጥሮ ስሜት እንደሚኖሩና አእምሮ እንደሌላቸው እንስሶች ናቸው፤ እንስሶች እንደሚጠፉ እነርሱም ፈጽመው ይጠፋሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos