Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ሳሙኤል 22:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ከዚህም በኋላ ሳኦል የካህናት ከተማ በሆነችው በኖብ የሚኖሩት ሁሉ ወንዶችና ሴቶች፥ ልጆችና ሕፃናት፥ የቀንድ ከብቶችና አህዮች፥ እንዲሁም የበግ መንጋዎች ሁሉ እንዲገደሉ አደረገ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 የካህናቱንም ከተማ ኖብን በሰይፍ መታት፣ በዚያ የሚኖሩትንም ወንዶችንና ሴቶችን፣ ልጆችንና ጡት የሚጠቡ ሕፃናትን፣ እንዲሁም በሬዎችንና አህያዎችን፣ በጎችንም ሁሉ በሰይፍ ስለት ፈጃቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 የካህናቱንም ከተማ ኖብን በሰይፍ መታት፥ በዚያ የሚኖሩትንም ወንዶችንና ሴቶችን፥ ልጆችንና ጡት የሚጠቡ ሕፃናትን፥ እንዲሁም በሬዎችንና አህያዎችን፥ በጎችንም ሁሉ በሰይፍ ስለት አስገደለ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 የካ​ህ​ና​ቱ​ንም ከተማ ኖብን በሰ​ይፍ ስለት መታ፤ ወን​ዶ​ች​ንና ሴቶ​ች​ንም፥ ብላ​ቴ​ኖ​ች​ንና ጡት የሚ​ጠ​ቡ​ትን፥ በሬ​ዎ​ች​ንና አህ​ዮ​ች​ንም፥ በጎ​ች​ንም በሰ​ይፍ ስለት ገደለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 የካህናቱም ከተማ ኖብን በሰይፍ ስለት መታ፥ ወንዶችንና ሴቶችንም፥ ብላቴኖችንና ጡት የሚጠቡትን፥ በሬዎችንና አህዮችንም በጎችንም በሰይፍ ስለት ገደለ።

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 22:19
13 Referencias Cruzadas  

ሄደህ በዐማሌቃውያን ላይ አደጋ በመጣል ያላቸውን ሁሉ ደምስስ፤ ከእነርሱ ምንም ነገር አታስቀር፤ ወንዶችን፥ ሴቶችን፥ ልጆችንና ሕፃናትን፥ ከብቶችን፥ በጎችን፥ ግመሎችንና አህዮችን ሁሉ ግደል።”


የእግዚአብሔር ፍርድ ምሕረት ለማያደርግ ሰው ምሕረት አያደርግም፤ ሆኖም ምሕረት ፍርድን ያሸንፋል።


በሕዝባችሁ ላይ ከባድ ጦርነት ይመጣል፤ ምሽጎቻችሁ ሁሉ ይፈራርሳሉ፤ ይህም ንጉሥ ሸልማን የቤትአርቤልን ከተማ በጦርነት እንዳፈራረሰና እናቶችን ከልጆቻቸው ጋር በምድር ላይ ፈጥፍጦ እንደ ጨረሰበት ጊዜ ይሆናል።


ዛሬ ጠላት በኖብ ከተማ የሚገኝ ሲሆን፥ የኢየሩሳሌም ከተማ በሆነችው በጽዮን ኰረብታ ላይ ለማስፈራራት ክንዱን እየነቀነቀ ነው።


ዐናቶት፥ ኖብ፥ ዓናንያ፥


ስለዚህም ንጉሥ ሳኦል ወደ ካህኑ የአሒጡብ ልጅ ወደ ሆነው ወደ አቤሜሌክና በኖብ ወደሚገኙት ዘመዶቹ ወደሆኑት ካህናት ሁሉ መልእክት ላከ፤ እነርሱም መጡ፤


በዚህን ጊዜ ከባለሥልጣኖቹ ጋር ኤዶማዊው ዶይቅ እዚያ ቆሞ ስለ ነበር “እኔ የእሴይን ልጅ በኖብ ወደሚገኘው የአሒጡብ ልጅ ወደ ሆነው ወደ አቤሜሌክ በመጣ ጊዜ አይቼዋለሁ፤


ዳዊት በኖብ ወደሚገኘው ወደ ካህኑ አቤሜሌክ ዘንድ ሄደ፤ አቤሜሌክም በፍርሃት እየተንቀጠቀጠ ሊቀበለው ወጥቶ “ማንም ሰው ሳይከተልህ ብቻህን ስለምን ወደዚህ መጣህ?” ሲል ጠየቀው።


ነገር ግን ሳኦልና ሠራዊቱ የአጋግን ሕይወት አተረፉ፤ እንዲሁም ምርጥ ምርጥ የሆኑትን በጎችና የቀንድ ከብቶች፥ የሰቡ ሰንጋዎችንና ጠቦቶችን ከዚህም ጋር መልካም የሆነውን ነገር ሁሉ አላጠፉም፤ እነርሱም ያጠፉት የማይረባውንና የማይጠቅመውን ነገር ብቻ ነበር።


ሰይፋቸውንም መዘው በከተማይቱ የተገኘውን ወንዱንም ሴቱንም ወጣቱንና ሽማግሌውን ሁሉ ገደሉ፤ የከብት፥ የበግና የአህያውን መንጋ ሁሉ ፈጁ።


“በከተማይቱና በውስጡ ያለው ነገር ሁሉ ለእግዚአብሔር የተረገመ ሆኖ መደምሰስ አለበት፤ ሴትኛ ዐዳሪዋ ግን የላክናቸውን ሰላዮች ደብቃ ስላዳነች መትረፍ የሚገባቸው እርስዋና ከእርስዋ ጋር በቤትዋ ያሉት ብቻ ናቸው።


ስለዚህ ኢየሱስን “እነዚህ ሕፃናት የሚሉትን ትሰማለህን?” አሉት፤ እርሱም “አዎ፥ እሰማለሁ፤ ‘ከልጆችና ከሚጠቡት ሕፃናት አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ’ የሚለውን ከቶ አላነበባችሁምን?” አላቸው፤


የዐማሌቅ ንጉሥ የነበረውን አጋግን በሕይወት ማርኮ፥ ሕዝቡን ሁሉ በሰይፍ ፈጀ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios