Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ሳሙኤል 14:44 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

44 ሳኦልም “እግዚአብሔር ይፍረድብኝ፤ አንተ ከሞት ቅጣት አታመልጥም!” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

44 ሳኦልም፣ “ዮናታን፣ አንተ ካልተገደልህ እግዚአብሔር ይፍረድብኝ፣ የከፋም ነገር ያምጣብኝ” አለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

44 ሳኦልም፥ “ዮናታን፥ እግዚአብሔር እንዲህ ያድርግብኝ፤ እንዲህም ይጨምርብኝ፤ ዛሬ ፈጽመህ ትሞታለህ” አለ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

44 ሳኦ​ልም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ያድ​ር​ግ​ብኝ፤ እን​ዲ​ህም ይጨ​ም​ር​ብኝ፤ ዛሬ ፈጽ​መህ ትሞ​ታ​ለህ” አለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

44 ሳኦልም፦ እግዚአብሔር እንዲህ ያድርግብኝ እንዲህም ይጨምርብኝ፥ ዮናታን ሆይ፥ ፈጽመህ ትሞታለህ አለ።

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 14:44
11 Referencias Cruzadas  

በሦስተኛው ወር ገደማ ሰዎች “ምራትህ ትዕማር የዝሙት ሥራ ፈጸመች፤ ከዚህም የተነሣ ፀንሳለች” ብለው ለይሁዳ ነገሩት። ይሁዳም “ወደ ውጪ አውጥታችሁ በእሳት አቃጥላችሁ ግደሉአት” አለ።


ሰዎቹም በመጋዝ፥ በብረት ዶማና በብረት መጥረቢያ እንዲሠሩ አደረጋቸው፤ ጡብ እንዲሠሩለትም አስገደዳቸው፤ በሌሎቹ የዐሞን ከተሞች ሁሉ ያሉትን ሰዎችም እንዲሁ በዚሁ ዐይነት እንዲሠሩ አደረጋቸው፤ ከዚህ በኋላ እርሱና ሠራዊቱ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።


ዳዊት በሀብታሙ ሰው ታሪክ እጅግ ተቈጥቶ “ይህን ያደረገው ሰው ሞት እንደሚገባው በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ!


እንዲሁም ለዐማሳ ሲናገር “አንተም ለእኔ የሥጋ ዘመድ ነህ፤ ከአሁን ጀምሮ በኢዮአብ ምትክ የሠራዊቴ አዛዥ አደርግሃለሁ፤ ይህንንም ባላደርግ እግዚአብሔር በሞት ይቅጣኝ!” ብላችሁ ንገሩት ሲል አዘዛቸው።


እግዚአብሔር መንግሥትን ከሳኦል ቤት ወሰደ የዳዊትን ዙፋን በእስራኤልና በይሁዳ ላይ ከሰሜን ከዳን ጀምሮ እስከ ደቡብ እስከ ቤርሳቤህ ድረስ ለመዘርጋት በመሐላ ቃል በገባለት መሠረት ባላስፈጽም በእኔ ላይ እግዚአብሔር ይፍረድ!”


ሲበዛ እንዳያስጠላህ ከሚያስፈልግህ በላይ ብዙ ማር. አትብላ፤


ባያትም ጊዜ በሐዘን ልብሱን በመቅደድ “ወዮ ልጄ! ልቤን በሐዘን ሰበርሽው! ለታላቅ ጭንቀትም ዳረግሽኝ፤ ለእግዚአብሔር ቃል ገብቼአለሁና ስለቴን ልመልሰውም አልችልም፤” አለ።


በምትሞቺበት እሞታለሁ፤ በምትቀበሪበትም እቀበራለሁ፤ ከሞት በቀር ከአንቺ የሚለየኝ ነገር ቢኖር እግዚአብሔር ይፍረድብኝ!”


በደል ሠርቶ የተገኘው ሰው ልጄ ዮናታን እንኳ ቢሆን በሞት እንደሚቀጣ ለእስራኤል ድልን በሰጠው በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ።” ነገር ግን አንዳች መልስ የሰጠው ሰው አልተገኘም።


ከመንጋቱ በፊት የእርሱ የሆኑትን ወንዶች ሁሉ አንድ እንኳ ሳላስቀር በሙሉ ሳልገድል ብቀር እግዚአብሔር እኔን በሞት ይቅጣኝ!”


ዔሊም “እግዚአብሔር የነገረህ ቃል ምንድን ነው? ከእኔ ምንም ነገር አትደብቅ፤ አንዳች ነገር ብትደብቅ እግዚአብሔር በአንተ ላይ ብርቱ ቅጣት ያምጣብህ” አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos