1 ሳሙኤል 14:36 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም36 ሳኦልም ወታደሮቹን “እንግዲህ እንውረድና በፍልስጥኤማውያን ላይ በሌሊት አደጋ እንጣልባቸው፤ እስኪነጋም ድረስ ሀብታቸውን ዘርፈን ሁሉንም እንፍጃቸው” አለ። እነርሱም “መልካም መስሎ የታየህን ሁሉ አድርግ” አሉት። ካህኑ ግን “በመጀመሪያ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንጠይቅ” አለ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም36 ሳኦልም፣ “ፍልስጥኤማውያንን ተከትለን በሌሊት እንውረድና እስኪነጋ ድረስ እንበዝብዛቸው፤ አንድም ሰው በሕይወት አናስቀርላቸው” አለ። እነርሱም፣ “መልካም መስሎ የታየህን ሁሉ አድርግ” ብለው መለሱለት። ካህኑ ግን፣ “እዚሁ እግዚአብሔርን እንጠይቅ” አለ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)36 ከዚያም በኋላ ሳኦልም፥ “ፍልስጥኤማውያንን ተከትለን በሌሊት እንውረድና እስኪ ነጋ ድረስ እንዝረፋቸው፤ አንድም ሰው በሕይወት አናስቀርላቸው” አለ። እነርሱም “መልካም መስሎ የታየህን ሁሉ አድርግ” ብለው መለሱለት። ካህኑ ግን፥ “ወደ እግዚአብሔር እንቅረብ” አለ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)36 ሳኦልም፥ “ፍልስጥኤማውያንን በሌሊት ተከትለን እንውረድ፤ እስኪነጋም ድረስ እንበዝብዛቸው፤ አንድ ሰው እንኳ አናስቀርላቸው” አለ። እነርሱም፥ “ደስ የሚያሰኝህን ሁሉ አድርግ” አሉት። ካህኑም፥ “ወደ እግዚአብሔር እንቅረብ” አለ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)36 ሳኦልም፥ ፍልስጥኤማውያንን በሌሊት ተከትለን እስኪነጋ ድረስ እንበዝብዛቸው አንድ ሰው እንኳ አናስቀርላቸው አለ። እነርሱም፦ ደስ የሚያሰኝህን ሁሉ አድርግ አሉት። ካህኑም፦ ወደ እግዚአብሔር እንቅረብ አለ። Ver Capítulo |