Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ጴጥሮስ 4:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ከእናንተ ማንም መከራ ሲቀበል እንደ ነፍሰ ገዳይ፥ እንደ ሌባ፥ እንደ ወንጀለኛ፥ በሰው ጉዳይ ጣልቃ እንደሚገባ አይሁን።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ከእናንተ ማንም መከራን የሚቀበል ቢኖር፣ ነፍሰ ገዳይ ወይም ሌባ ወይም ወንጀለኛ ወይም በሰው ነገር ጣልቃ ገቢ ሆኖ መከራን አይቀበል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ማንም ከእናንተ መካከል እንደ ነፍሰ ገዳይ፥ ወይም እንደ ሌባ፥ ወይም እንደ ክፉ አድራጊ፥ ወይም በሌሎች ጉዳይ ጣልቃ እንደሚገባ ሆኖ መከራ የሚቀበል አይኑር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ከእናንተ ማንም ነፍሰ ገዳይ ወይም ሌባ ወይም ክፉ አድራጊ እንደሚሆን ወይም በሌሎች ጉዳይ እንደሚገባ ሆኖ መከራን አይቀበል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ከእናንተ ማንም ነፍሰ ገዳይ ወይም ሌባ ወይም ክፉ አድራጊ እንደሚሆን ወይም በሌሎች ጉዳይ እንደሚገባ ሆኖ መከራን አይቀበል፤

Ver Capítulo Copiar




1 ጴጥሮስ 4:15
9 Referencias Cruzadas  

ይህን ያልንበት ምክንያት በመካከላችሁ አንዳንድ ሥራ ፈቶች እንዳሉ በመስማታችን ነው፤ እነዚህ ሰዎች በማያገባቸው ነገር እየገቡ ሌሎችን ከማወክ በቀር ምንም አይሠሩም።


በጸጥታም ለመኖር እንድትጣጣሩ እና የራሳችሁን ጉዳይ እንድታስቡ ከዚህ በፊት እንዳዘዝናችሁም በገዛ እጃችሁ እንድትሠሩ ነው።


ደግሞም ሥራ መፍታትን ይማራሉ፤ ሥራ መፍታት ብቻ ሳይሆን በየሰዉ ቤት እየዞሩ ሰውን የሚያሙ፥ በሰው ነገር የሚገቡና መናገር የማይገባቸውን የሚናገሩ ይሆናሉ።


የእግዚአብሔር ፈቃድ ከሆነ እናንተ ክፉ ነገርን በማድረግ መከራ ከምትቀበሉ መልካም ነገርን በማድረግ መከራ ብትቀበሉ ይሻላል።


በዚህም ወንጌል ምክንያት እንደ ወንጀለኛ በሰንሰለት ታስሬ መከራ እቀበላለሁ፤ የእግዚአብሔር ቃል ግን አይታሰርም።


“በእኔ ምክንያት ሰዎች ሲሰድቡአችሁና ሲያሳድዱአችሁ፥ በውሸትም ስማችሁን ሲያጠፉት ደስ ይበላችሁ።


ሌባው የሰረቀውን ይመልስ፤ የሚከፍለው ቢያጣ በባሪያነት ይሸጥ፤ የሰረቀው እንስሳ ላምም ቢሆን፥ አህያም ቢሆን፥ ወይም በግ ቢሆንና በሕይወት በእጁ ቢገኝ ለያንዳንዱ እንስሳ እጥፍ ዋጋ ይክፈል። “አንድ ሌባ ቤት ሰብሮ ሲገባ ቢያዝና ተመትቶ ቢገደል ተከላካዩ ለደሙ ተጠያቂ አይሆንም። ሌባው ሰብሮ የገባው ፀሐይ ከወጣ በኋላ ሆኖ ተመትቶ ቢገደል ግን ተከላካዩ ለደሙ ተጠያቂ ይሆናል።


መልካም ነገር በማድረግ መከራን ብትቀበሉ እንኳ በረከትን ታገኛላችሁ፤ የሰዎችን ዛቻ አትፍሩ፤ አትጨነቁም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios