9 በእምነታችሁም የምትጠብቁትን የነፍሳችሁን መዳን ታገኛላችሁ።
9 የእምነታችሁን ፍጻሜ፣ እርሱም የነፍሳችሁን ድነት እየተቀበላችሁ ነውና።
9 የእምነታችሁን ፍፃሜ እርሱም የነፍሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ ነውና።
አሁን ግን ከኃጢአት ባርነት ነጻ ወጥታችሁ የእግዚአብሔር አገልጋዮች በመሆናችሁ ቅድስናን ታገኛላችሁ፤ የቅድስናም መጨረሻ የዘለዓለም ሕይወት ነው።
እነዚህ ሁሉ በእምነት እንዳሉ ሞቱ፤ እግዚአብሔር ሊሰጣቸው ቃል የገባላቸውንም ነገር አላገኙም፤ ነገር ግን ከሩቅ አይተው ልክ እንዳገኙት አድርገው በደስታ ተቀበሉት። በምድር ላይ እንግዶችና መጻተኞች መሆናቸውንም ተገነዘቡ።
ስለዚህ ርኲሰትንና የክፋትንም ብዛት ሁሉ አስወግዳችሁ እግዚአብሔር በልባችሁ የተከለውንና ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን ቃል በትሕትና ተቀበሉ።
እነዚህ በወህኒ ቤት የነበሩ መናፍስት ቀድሞ በኖኅ ዘመን መርከብ ሲዘጋጅ እግዚአብሔር በትዕግሥት ሲጠብቃቸው ሳለ አንታዘዝም ያሉ ናቸው። በዚያ መርከብ ውስጥ ገብተው በውሃ አማካይነት የዳኑት ቊጥራቸው ስምንት የሆነ ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው።