Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 8:51 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

51 እነርሱ እኮ እንደ እቶን እሳት ከምታቃጥል ከግብጽ ምድር ያወጣሃቸው ሕዝብህ ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

51 ከዚያች እንደ ብረት ማቅለጫ እቶን እሳት ከሆነችው፣ ከግብጽ ምድር ያወጣሃቸው ሕዝብህም ርስትህም ናቸውና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

51 እነርሱ እኮ እንደ እቶን እሳት ከምታቃጥል ከግብጽ ምድር ያወጣሃቸው ሕዝብህ ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

51 ከግ​ብጽ ምድር ከብ​ረት እቶን ውስጥ ያወ​ጣ​ሃ​ቸው ሕዝ​ብ​ህና ርስ​ትህ ናቸ​ውና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

51 ከግብጽ ምድር ከብረት እቶን ውስጥ ያወጣሃቸው ሕዝብህና ርስትህ ናቸውና።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 8:51
15 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! የቀድሞ አባቶቻችንን ከግብጽ ምድር ባወጣህ ጊዜ ከዓለም ሕዝብ ሁሉ መካከል እስራኤልን የራስህ ሕዝብ እንዲሆን የመረጥከው መሆኑን በአገልጋይህ በሙሴ አማካይነት ተናግረሃል።”


ጸሎታቸውን ስማ፤ በመኖሪያህ በሰማይ ሆነህ ጸሎታቸውን በመስማትም ምሕረት አድርግላቸው፤ የሕዝብህን ኃጢአት ሁሉ ይቅር በል።


“እግዚአብሔር ሆይ! እነዚህ የአንተ አገልጋዮችና የገዛ ሕዝብህ ናቸው፤ ከዚህ በፊትም በታላቁ ኀይልህና በብርቱ ክንድህ በመታደግ አድነሃቸዋል።


አምላክ ሆይ! ሕዝብህን አድን፤ የአንተ የሆኑትንም ባርክ፤ እረኛቸውም ሁን፤ ለዘለዓለምም ተንከባከባቸው።


እንደ ብር ሳይሆን በመከራ እሳት አንጥሬአችኋለሁ፥ በችግር እቶንም ፈትኜአችኋለሁ።


አምላክ ሆይ! አምርረህ አትቈጣ፤ ኃጢአታችንንም ለዘለዓለም አታስብብን፤ እኛ ሁላችን ሕዝብህ መሆናችንን አስታውስ።


ይህ ቃል ኪዳን እንደ ጋለ ምድጃ ከሆነችባቸው አገር ከግብጽ ባወጣኋቸው ጊዜ ለቀድሞ አባቶቻችሁ የሰጠሁት ነው፤ ለእኔ እንዲታዘዙና እኔ የምላቸውን ሁሉ እንዲፈጽሙ ነገርኳቸው፤ የሚታዘዙኝም ከሆነ እነርሱ ሕዝቤ እንደሚሆኑና እኔም አምላካቸው እንደምሆን ገለጥኩላቸው።


የያዕቆብ አምላክ ግን እንደ እነርሱ አይደለም፤ እርሱ የሁሉ ነገር ፈጣሪ ነው፤ ለራሱ የተለየ ሕዝብ እንዲሆን እስራኤልን መርጦታል፤ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።


ናቡከደነፆር ወደሚነደው የእሳት ነበልባል ጒድጓድ ተጠግቶ “የልዑል አምላክ አገልጋዮች የሆናችሁ እናንተ ሲድራቅ፥ ሚሳቅና አብደናጎ ሆይ! ወጥታችሁ ወደዚህ ኑ!” በማለት ተጣራ፤ እነርሱም ከእሳቱ ወጡ።


እስራኤል የእግዚአብሔር ድርሻ ነው፤ ያዕቆብም አንጡራ ሀብቱ ነው።


እናንተ ግን እሳት እንደሚነድበት የብረት ምድጃ ከሆነችው ከግብጽ መንጥቆ እግዚአብሔር ያወጣችሁ ዛሬ እንደ ሆናችሁት ሁሉ ለራሱ የተለያችሁ ወገኖቹ እንድትሆኑ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos