Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 7:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 የገንዳው ጐኖች ውፍረት አንድ መዳፍ ነበር፤ የጽዋ ቅርጽ ያለው አበባ የሚመስል የአፉ ክፈፍ የአሸንድዬ አበባ ቅርጽ ነበረው፤ ይህም ገንዳ አርባ ሺህ ሊትር ያኽል ውሃ የሚይዝ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 የገንዳው ውፍረት አንድ ስንዝር ሲሆን፣ የከንፈሩ ጠርዝ ደግሞ የአበባ ቅርጽ ያለው የጽዋ ከንፈር የመሰለ ነው፤ ይህም ሁለት ሺሕ የባዶስ መስፈሪያ ያህል ውሃ የሚይዝ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 የገንዳው ጐኖች ውፍረት አንድ መዳፍ ነበር፤ የጽዋ ቅርጽ ያለው አበባ የሚመስል የአፉ ክፈፍ የአሸንድዬ አበባ ቅርጽ ነበረው፤ ይህም ገንዳ አርባ ሺህ ሊትር ያኽል ውሃ የሚይዝ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ውፍ​ረ​ቱም አንድ ጋት ነበረ። ከን​ፈ​ሩም እንደ ጽዋ ከን​ፈር ተሠ​ርቶ ነበር፤ እንደ ሱፍ አበ​ባ​ዎች ሆኖ ተከ​ር​ክሞ ነበር። ሁለት ሺህም የባ​ዶስ መስ​ፈ​ሪያ ይይዝ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ውፍረቱም አንድ ጋት ነበረ፤ ከንፈሩም እንደ ጽዋ ከንፈር ተሠርቶ ነበር፤ እንደ ሱፍ አበባዎች ሆኖ ተከርክሞ ነበር። ሁለት ሺህም የባዶስ መስፈሪያ ይይዝ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 7:26
12 Referencias Cruzadas  

የሊባኖስ ዛፍ እንጨት ሳንቃዎች በአበባ እንቡጦችና በፈኩ አበባዎች ቅርጽ አጊጠው ነበር፤ ውስጡም ሁሉ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት ተጠርቦ በተሠራ ሳንቃ ስለ ተለበደ የግንቡ ድንጋዮች አይታዩም ነበር።


ሁለቱን በሮች በኪሩቤል፥ በዘንባባ ዛፎችና በፈኩ የአበባ ቅርጾች አስጌጣቸው፤ እርሱም በሮቹን፥ ኪሩቤልን፥ የዘንባባ ዛፎቹን፥ ቅርጾቹንም በወርቅ ለበጣቸው።


እነርሱንም ሙሉ በሙሉ በወርቅ በተለበጡ በኪሩቤል፥ በዘንባባ ዛፎችና በፈኩ የአበባ ቅርጾች አስጌጣቸው።


በመመላለሻው ምሰሶዎች አናት ላይ ያሉት ጒልላቶች ቁመታቸው አንድ ሜትር ከሰማንያ ሳንቲ ሜትር ሲሆን የአሸንድዬ አበባን በሚመስል ሥራ ተጊጠው ነበር፤


ገንዳውም ከነሐስ በተሠሩ ዐሥራ ሁለት የበሬዎች ምስሎች ጀርባ ላይ ተቀመጠ፤ ኰርማዎቹም በየአቅጣጫው ፊታቸውን ወደ ውጪ መልሰው ሦስቱ ወደ ሰሜን፥ ሦስቱ ወደ ደቡብ፥ ሦስቱ ወደ ምሥራቅ ሦስቱ ወደ ምዕራብ የሚመለከቱ ይመስሉ ነበር።


ሑራም የእያንዳንዱ ርዝመት አንድ ሜትር ከሰማንያ ሳንቲ ሜትር፥ ወርዱ አንድ ሜትር ከሰማንያ ሳንቲ ሜትር፥ ቁመቱ አንድ ሜትር ከሠላሳ ሳንቲ ሜትር የሆነ ዐሥር ባለመንኰራኲር የዕቃ ማስቀመጫዎችን ከነሐስ ሠራ።


ሑራም ለእያንዳንዱ የዕቃ ማስቀመጫ ዐሥር መታጠቢያ ገንዳዎች ሠራ፤ እያንዳንዱ ገንዳ ዙሪያ አጋማሽ ስፋት አንድ ሜትር ከሰማንያ ሳንቲ ሜትር ያኽል ሲሆን፥ ስምንት መቶ ሊትር ያኽል ውሃ ይይዝ ነበር፤


የሁሉም ጀርባቸው ወደ ውስጥ ነበር። የገንዳው ጐኖች ውፍረት ሰባ አምስት ሚሊ ሜትር ሲሆን፥ ክፈፉም እንደ ኩባያ ክፈፍ ሆኖ እንደ አሸንድዬ አበባ ወደ ውጪ የተቀለበሰ ነው፤ በርሜሉ ሥልሳ ሺህ ሊትር ያኽል ውሃ የሚይዝ ነበር።


በዙሪያው ሰባ አምስት ሳንቲ ሜትር ስፋት የሚሆን ጠርዝ አብጅለት፤ በጠርዙም ዙሪያ የወርቅ ክፈፍ አድርግለት።


ሁለቱ ዐምዶች አንድ ዐይነት ቅርጽ ያላቸው ሆነው እያንዳንዳቸው ስምንት ሜትር ቁመትና አምስት ሜትር የሚያኽል ዙሪያ ነበራቸው፤ ውስጣቸውም ክፍት ነበር፤ ብረቱም ሰባ አምስት ሚሊ ሜትር ውፍረት ነበረው፤


“የመስፈሪያዎች ሁሉ አማካኝ መለኪያ ጎሞር ይሁን፤ የደረቅ ነገሮች መስፈሪያ የሆነው ኢፍ፥ የፈሳሽ ነገሮች መለኪያ ከሆነው ባት ጋር እኩል መሆን አለበት፤ በዚህም ዐይነት አንድ ጎሞር ከዐሥር ኤፋና ከዐሥር ባት ጋር እኩል ይሆናል።


ከዘይትም የተመደበው ከያንዳንዱ ቆሮስ አንድ ዐሥረኛ ባት ነው። (አንድ ቆሮስ፥ አንድ ጎሞር ወይም ዐሥር ባት ማለት ነው)


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos