የሑራም አቢ እናት ከዳን ነገድ ስትሆን፥ አባቱም የጢሮስ ተወላጅ ነው፤ ሑራም አቢ ከወርቅ፥ ከብር፥ ከነሐስ፥ ከብረት፥ ከድንጋይና ከእንጨት ልዩ ልዩ ነገሮችን የመሥራት ችሎታ አለው፤ እንዲሁም ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ጨርቅና ከበፍታ የተለያየ ልብስ መሥራት ይችላል፤ ከዚህም ሌላ ልዩ ልዩ ቅርጽ ማውጣትና በተሰጠውም ንድፍ መሠረት ሁሉን ነገር መሥራት ይችላል፤ ስለዚህ ይህን ሰው በእጅ ሥራ ከሠለጠኑ ከአንተ ሰዎችና ከእነዚያ ለአባትህ ይሠሩ ከነበሩ ሰዎች ጋር እንዲሠራ አድርገው።