Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 20:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 አሁን ደግሞ ቤተ መንግሥትህንና የባለሥልጣኖችህን ቤት ሁሉ በርብረው ዋጋ ያለውን ንብረት ሁሉ ይዘው እንዲመጡ የጦር መኰንኖቼን እልካለሁ፤ እነርሱም ነገ ጧት በዚሁ ሰዓት እዚያ ይደርሳሉ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ሆኖም ነገ በዚሁ ጊዜ ቤተ መንግሥትህንና የሹማምትህን ቤቶች እንዲበረብሩ፣ ሹማምቴን እልካቸዋለሁ። እነርሱም ማንኛውንም ለአንተ ዋጋ ያለውን ሁሉ በእጃቸው በማስገባት ይወስዱታል።’ ”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 አሁን ደግሞ ቤተ መንግሥትህንና የባለሥልጣኖችህን ቤት ሁሉ በርብረው ዋጋ ያለውን ንብረት ሁሉ ይዘው እንዲመጡ የጦር መኰንኖቼን እልካለሁ፤ እነርሱም ነገ ጧት በዚሁ ሰዓት እዚያ ይደርሳሉ።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እር​ሱም፥ “ኢይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊ​ውን ናቡ​ቴን፦ የወ​ይ​ን​ህን ቦታ በገ​ን​ዘብ ስጠኝ፤ ወይም ብት​ወ​ድድ በፋ​ን​ታው ሌላ የወ​ይን ቦታ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ ብዬ ተና​ገ​ር​ሁት፤ እርሱ ግን የአ​ባ​ቶ​ቼን ርስት አል​ሰ​ጥ​ህም ስለ አለኝ ነው” አላት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 እርሱም “ኢይዝራኤላዊውን ናቡቴን ‘የወይንህን ቦታ በገንዘብ ስጠኝ፤ ወይም ብትወድድ በፋንታው ሌላ የወይን ቦታ እሰጥሃለሁ፤’ ብዬ ተናገርሁት፤ እርሱ ግን ‘የወይን ቦታዬን አልሰጥህም፤’ ብሎ ስለ መለሰልኝ ነው፤” አላት።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 20:6
13 Referencias Cruzadas  

የታላቁ ልጅዋን የዔሳውን የክት ልብስ ከተቀመጠበት ቦታ አውጥታ ለያዕቆብ አለበሰችው።


ዳዊትም “እነሆ እኔ ለምርጫ በሚያስቸግር ሁኔታ ላይ ነኝ! ይሁን እንጂ በሰው እጅ መውደቅ አልፈልግም፤ እግዚአብሔር መሐሪ ስለ ሆነ እርሱ ራሱ ይቅጣኝ!” አለ።


ከጥቂት ጊዜም በኋላ እነዚያው መልእክተኞች ከንጉሥ ቤንሀዳድ ሌላ ትእዛዝ ይዘው እንደገና ወደ አክዓብ መጡ፤ ትእዛዙም እንዲህ የሚል ነበር፤ “ብርህንና ወርቅህን፥ ሚስቶችህንና ልጆችህን እንድታስረክበኝ መልእክት ልኬብህ እንደ ነበር ይታወሳል፤


ንጉሥ አክዓብም የሀገሪቱን ሽማግሌዎች ሁሉ ጠርቶ “ይህ ሰው ምን ዐይነት ጠብ እንደሚፈልግ ተመልከቱ። ከዚህ በፊት ሚስቶቼንና ልጆቼን፥ ብሬንና ወርቄን እንዳስረክበው ጠይቆኝ ተስማምቼ ነበር” አላቸው።


ጣዖቶችን የሚሠሩ ሁሉ ከንቱ ናቸው፤ ከፍተኛ ግምት የሚሰጡአቸው ጣዖቶቻቸውም ዋጋቢሶች ናቸው፤ በዚህም ኀፍረት ይደርስባቸዋል።


“እናንተ መሪዎች አልቅሱ፤ እናንተ የሕዝብ ጠባቂዎች ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ‘ዋይ፥ ዋይ!’ በሉ፤ በዐመድ ላይ እየተንከባለላችሁ እዘኑ፤ ሁላችሁም የምትታረዱበት ጊዜ ደርሶአል፤ ውድ የሆነ የሸክላ ዕቃ ሲወድቅ ተሰብሮ እንደሚበታተን፥ እናንተም ትበታተናላችሁ።


የኢየሩሳሌም ሕዝብ ጠላቶች ከፍተኛ ዋጋ ያላቸውን የሕዝቡን ሀብት ዘረፉ፤ ወደ እግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ እንዳይገቡ የተከለከሉ አሕዛብ እንኳ ቤተ መቅደስዋን ሲወሩ ታዩ።


የኢየሩሳሌም ሕዝብ በቀድሞ ጊዜ የነበሩአቸውን የከበሩ ነገሮች በችግራቸውና በጭንቀታቸው ቀን ያስታውሳሉ፤ እነርሱም በጠላት እጅ በወደቁ ጊዜ፥ አንድም ረዳት ባልነበራቸው ጊዜ፥ ጠላቶቻቸው የከተማቸውን ውድቀት ተመልክተው ተሳለቁባቸው።


በወንድሞቹ መካከል ፍሬያማ ቢሆንም የእግዚአብሔር ቅጣት የሆነው የምሥራቁ ነፋስ ከምድረ በዳ ተነሥቶ ይመጣል፤ ምንጩ ይቆማል፤ ወንዙም ይደርቃል። ነፋሱም የነበሩትን ውድ ዕቃዎች ሁሉ ገፎ ይወስድበታል።


ብሬንና ወርቄን እንዲሁም ውድ የሆነ ሀብቴን ሁሉ ወስዳችሁ ወደ ጣዖት ማምለኪያ ቤታችሁ አስገብታችኋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos