Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ነገሥት 20:33 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 የንጉሥ ቤንሀዳድ ባለሟሎች የምሕረት መልእክት ይጠባበቁ ስለ ነበር፥ አክዓብ “ወንድሜ” ሲል በሰሙ ጊዜ ወዲያውኑ ቀበል አድርገው “አንተ እንዳልከው ቤንሀዳድ በእርግጥ ወንድምህ ነው!” አሉት። አክዓብም “ወደ እኔ አምጡት!” አላቸው። ቤንሀዳድም በመጣ ጊዜ፥ አክዓብ ወደ ሠረገላው ገብቶ እንዲቀመጥ ቤንሀዳድን ጋበዘው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 ሰዎቹም ይህን በደግ በመተርጐም ቃሉን ከአፉ ቀበል አድርገው፤ “አዎን ቤን ሃዳድ ወንድምህ ነው” አሉት። ንጉሡም፣ “በሉ ሂዱና አምጡት” አላቸው፤ ቤን ሃዳድም በመጣ ጊዜ፣ አክዓብ ሠረገላው ላይ እንዲወጣ አደረገው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 የንጉሥ ቤንሀዳድ ባለሟሎች የምሕረት መልእክት ይጠባበቁ ስለ ነበር፥ አክዓብ “ወንድሜ” ሲል በሰሙ ጊዜ ወዲያውኑ ቀበል አድርገው “አንተ እንዳልከው ቤንሀዳድ በእርግጥ ወንድምህ ነው!” አሉት። አክዓብም “ወደ እኔ አምጡት!” አላቸው። ቤንሀዳድም በመጣ ጊዜ፥ አክዓብ ወደ ሠረገላው ገብቶ እንዲቀመጥ ቤንሀዳድን ጋበዘው።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 20:33
7 Referencias Cruzadas  

በዚህም ምክንያት ንጉሥ አሳ በቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥቱ የተረፈውን ወርቅና ብር ሁሉ በማውጣት በባለሟሎቹ እጅ፥ በደማስቆ ከተማ ለነበረው የጣብሪሞን ልጅ፥ የሔዝዮን የልጅ ልጅ ለሆነው ለሶርያ ንጉሥ ቤንሀዳድ ስጦታ አድርጎ ላከለት፤ ከስጦታውም ጋር እንዲህ የሚል መልእክት ነበረ፤


ከዚህም በኋላ እነርሱ በወገባቸው ማቅ ታጥቀው፥ በራሳቸውም ገመድ ጠምጥመው ወደ ንጉሥ አክዓብ በመሄድ “አገልጋይህ ቤንሀዳድ ምሕረት አድርገህ ሕይወቱን እንድታተርፍለት ይማጠንሃል” አሉት። አክዓብም “እርሱ እስከ አሁን በሕይወት አለ ማለት ነውን? ከሆነስ መልካም ነው፤ እንግዲህ እርሱ ለእኔ እንደ ወንድም ነው!” ሲል መለሰላቸው።


ቤንሀዳድም አክዓብን “አባቴ ከአባትህ የወሰዳቸውን ከተሞች እመልስልሃለሁ፤ አባቴ በሰማርያ እንዳደረገው ሁሉ አንተም በደማስቆ ለራስህ የንግድ ማእከል ልታቋቊም ትችላለህ” አለው። አክዓብም “እንግዲያውስ በዚህ ስምምነት መሠረት እኔም በነጻ እለቅሃለሁ” ሲል መለሰለት። አክዓብም በዚህ ዐይነት ከእርሱ ጋር የውል ስምምነት አድርጎ በነጻ እንዲሄድ ፈቀደለት።


ኢዩ ተነሥቶ እንደገና ጒዞ ቀጠለ፤ በመንገድ ሳለም የሬካብን ልጅ ኢዮናዳብን አገኘ፤ ኢዩም ሰላምታ ከሰጠው በኋላ “እኔና አንተ በሐሳብ አንድ ነን፤ ታዲያ ከእኔ ጋር ትተባበራለህን?” ሲል ጠየቀው። ኢዮናዳብም “አዎ እተባበርሃለሁ” ሲል መለሰ። ኢዩም “እንግዲያውስ ጨብጠኝ” ሲል መለሰለት፤ እጅ ለእጅ ተያይዘው ኢዩ ደግፎት በሠረገላው ላይ አስቀመጠውና፥


ቀዝቃዛ ውሃ በሙቀት ጊዜ የሚያረካውን ያኽል ታማኝ መልእክተኛም የላከውን ሰው ያረካል።


ጌታውም እምነት ያጐደለውን መጋቢ በብልኅነቱ አደነቀው፤ ይህም ከእግዚአብሔር ሰዎች ይልቅ የዓለም ሰዎች በዓለማዊ ኑሮአቸው ብልኆች መሆናቸውን ያሳያል።


ኢትዮጵያዊውም “የሚያስረዳኝ ሰው ሳይኖር እንዴት ሊገባኝ ይችላል?” አለና ፊልጶስን “ወደ ሠረገላው ውጣና ከእኔ ጋር ተቀመጥ” አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos